Daily Weather Report 25 September 14

Weather Summary for previous day

Sept. 13, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ መካከለኛው እና ምዕራብ አማራ፣ በምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ምስራቅና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሲዳማ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ደግሞ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over west, central, and west Amhara, west, central, east, and south Oromia, central Ethiopia, south Ethiopia, and Sidama. As a result, many places received light to moderate rainfall (1-29 mm); additionally, in Addis Ababa, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in 24 hours.

Weather Forecast for next day

Sept. 15, 2025

በነገው ዕለት ዝናብ ከደቡባዊ የህንድ ውቅያኖስ በመነሳት ወደ ሀገራችን የሚገባው ዕርጥበት አዘል የአየር ሁኔታ በተመሳሳይ መልኩ ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡ በመሆኑም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ፣ ካማሽ እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ሆሮጉድሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮሬ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሀሮ ሊሙ፣ ጊዳአያና፣ ጅማ አርጆ፣ ኑኑኩምባ፣ ሲቡሲሬ፣ ጎቡሰዮ፣ አቤዶንጎሮ፣ ባኮጢቤ፣ በደሌ፣ ያዩ፣ አሌ፣ ሰተማ፣ ኦሞናዳ፣ ሰቃ ጮቆርሳ፣ ኖኖቤንጃ፣ ማሻ፣ የኪ፣ ገሻ፣ ሳይለም፣ ጠምባሮ፣ ባዳዋቾ፣ ሀደሮ፣ ቦሎሶሶሬ፣ ቦናዙሪያ፣ አርቤጎና እና ኮኮሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, the humid weather that will enter our country from the southern Indian Ocean will continue in the same way. Hence, from Tigray region west, central, north west, south east, south and east zones; from Amhara region west, north, south and central Gondar, north, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from Benishangul Gumuz region Metekal, Asossa, Kamashi and Mao Komo zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, Horro Guduru, west and east Wellega, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Bale, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Gambella region Majang, Nuwer, Itang and Agnuwak zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro and Konta zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Kebena special zone, east Gurage, Mareko special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, south Omo, Kore and Gedeo zones; Sidama region zones and from Somali region Fafen zone will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm will be expected in Haro Limmu, Gidayana, Jimma Arjo, Nunu Kumba, Sibusire, Gobuseyo, Abedongoro, Bakotibe, Bedele, Yayu, Ale, Setema, Omo Nada, Seka Chekorsa, Nono Benja, Masha, Yeki, Gesha, Sayilem, Tembaro, Badawacho, Hadero, Bolososore, Bona Zuria, Arbegona, and Kokosa within 24 hours.