Daily Weather Report 25 September 13

Weather Summary for previous day

Sept. 12, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአይራ እና አርሲ ሮቤ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud cover was present over the parts of our country that benefited from the winter rains. As a result, many locations received light to moderate rainfall (1-29 mm). In addition, more than 30 mm of heavy rainfall was recorded in Aira and Arsi Robe within a 24-hour period.

Weather Forecast for next day

Sept. 14, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ዳንግላ፣ ጓንጓ፣ ሀሮ፣ ሲቡሲሬ፣ ዋማሀጋሎ፣ አርጆ፣ ደቦሀና፣ ዲዱ፣ ሰተማ፣ ያዮ፣ ጉማይ፣ ዳኖ፣ መስቃን፣ ሶሮ፣ ዱና፣ ሀደሮ፣ ጠምባሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover and accumulation over the Kiremt rain benefiting areas of our country. In this association with this, from Tigray region west, central, north west, south east, south and east zones; from Amhara region west, north, south and central Gondar, north, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, north Shewa and Waghemra zones; from Afar region Gabi zone; from Benishangul Gumuz region Metekel, Mao Komo, Asossa and Kamashi zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horro Guduru, Kelam, west and east Wellega, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Borena and east Borena, Bale and east Bale, west and east Hararge; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Gambella region Agnuak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the south west Ethiopia region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro and Konta; from the Central Ethiopia region Gurage, Silte, Kebena special zone, east Gurage, Mareko special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro; from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedeo zones; Sidama region zones and from Somali region Fafen zone will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, Dangla, Guangua, Haro, Sibusire, Wamahagalo, Arjo, Debohana, Didu, Setema, Yayo, Gumay, Dano, Meskan, Soro, Duna, Hadero, and Tembaro are expected to experience heavy rainfall exceeding 30 mm within a 24-hour period.