Daily Weather Report 25 September 12

Weather Summary for previous day

Sept. 11, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በ11 የሚያህሉ ቦታዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud cover and accumulation occurred in parts of our country that benefited from the Kiremt rains. In association with this, many places received light to moderate rainfall (1-29 mm). In addition, more than 30 mm of heavy rain was recorded in 11 places within a 24-hour period.

Weather Forecast for next day

Sept. 13, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀሪ እና ጋቢ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በመኮ፣ ጨዋቃ፣ ደዴሳ፣ ቦረቻ፣ ሊሙሰቃ፣ ጮራ፣ ጎማ፣ ዳኖ፣ ኖኖ፣ ባኮቲቤ፣ ጅባት፣ አመያ፣ ጋምቤላ፣ መንገሽ፣ ማሻ፣ ሸኮ፣ ዳሞትሶሬ፣ ሶዶ፣ ሁምቦ፣ ብላቴ፣ ቡርሳ፣ አሮሬሳ፣ ምዕራብ አባያ እና ወናጎ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡

For the coming day, there will be strong cloud cover and accumulation across the Kiremt rain-benefiting areas of our country. In this association with this, from Tigray region west, central, north west, south east, south and east zones; from Amhara region west, north, south and central Gondar, north, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo national special zone, north Shewa and Waghemra zones; from Afar region Kilbeti, Hari, Fanti, Gabi and Awusi zones; from Benishangul Gumuz region Metekal, Mao Komo, Asossa and Kamashi zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horro Guduru, Kelam, west and east Wellega, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Borena and east Borena, Bale and east Bale, west and east Hararge; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Gambella region Agnuak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the south west Ethiopia region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro and Konta; from the Central Ethiopia region Gurage, Silte, Kebena special zone, east Gurage, Mareko special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro; from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedeo zones; Sidama region zones and from Somali region Siti and Fafen zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, Sayonola, Anfilo, Darimu, Meko, Chwaka, Dedessa, Borecha, Limuska, Chora, Goma, Dano, Nono, Bakotibe, Jibat, Amaya, Gambella Zuriya, Mengesh, Masha, Sheko, Kachabra, Damotsore, Sodo Zuria, Humbo, Darara, Bilatte Zuriya, Bursa, Aroresa, Mirab Abaya, and Wenago will experience above 30 mm of heavy rainfall within a 24-hour.