Daily Weather Report 25 September 10
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ ክፍሎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል። በተጨማሪም በሽሬእንደስላሴ፣ ካቺሴ እና ሀሮ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, areas of the country that benefited from Kiremt rain had cloud coverage. Consequently, many places received light to moderate (1-29 mm) rain. Moreover, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Shire Endesilase, Kachise, and Haro in 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ሀሪ፣ ፋንቲ፣ ጋቢ እና አዉሲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በደባርቅ፣ ሊቦከምከም፣ ፎገራ፣ ፋርጣ፣ ጉባ፣ ዳንጉር፣ ወንበራ፣ ቡለን፣ መናሲቡ፣ ደዴሳ፣ ጎማ፣ ሰቃ ጮቆርሳ፣ ማንቾ፣ ቀርሳ፣ ኦሞናዳ፣ ሶኮሩ፣ ሊሙኮሳ፣ ቦቶርጦላይ፣ ሊሙሰቃ፣ ወንጭ፣ ኢሉ፣ ባቾ፣ አርሲ ነገሌ፣ ኮኮሳ፣ ዶዶላ፣ አበሸጌ፣ ለሞ፣ ሳንኩራ እና ዉልበርግ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For the coming day, areas of the country benefiting from Kiremt rain will have strong cloud coverage and accumulation. In this respect, from Tigray region west, central, north west, south east, south and east zones; from Amhara region west, north, south and central Gondar, north, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Oromo national special zone, north Shewa and Waghemra zones; from Afar region Kilbeti, Hari, Fanti, Gabi and Awusi zones; from Benishangul Gumuz region Metekal, Mao Komo, Asossa and Kamashi zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horro Guduru, Kelam, west and east Wellega, north, west, south west and east Shewa, Arsi and west Arsi, Guji and west Guji, Borena and east Borena, Bale and east Bale, west and east Hararge; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Gambella region Agnuak, Nuwer, Itang and Majang zones; from the south west Ethiopia region, Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro and Konta; from the Central Ethiopia region Gurage, Silte, Kebena special zone, east Gurage, Mareko special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro; from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedeo zones; Sidama region zones and from Somali region Siti and Fafen zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Besides, Debark, Libokemkem, Fogera, Farta, Guba, Dangur, Wenbera, Bulen, Mena Sibu, Dedesa, Gomma, Seka Chokorsa, Mancho, Kersa, Omo Nada, Sokoru, Limmukosa, Botortolay, Limuseka, Wenchi, Ilu, Bacho, Arsi Negelle, Kokosa, Dodola, Abeshege, Lemmo, Sankura, and Wulberg will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours.