Daily Weather Report 25 September 09

Weather Summary for previous day

Sept. 8, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት አካባቢዎች እና በደቡብ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቡለን፣ በሀሮ፣ ያንፋ እና ፅጌሬዳ 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud coverage over the Kiremt rain-benefiting areas and in the southern parts of our country. In this regardes, many places received light to moderate (1-29 mm) amount rainfall. Additionally, heavy rainfall exceeding 30mm within a 24-hour was recorded in Bullen, Haro, Yanfa, and Tsigereda within 24 hours.

Weather Forecast for next day

Sept. 10, 2025

በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብ፤ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የአውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጅ እና ምዕራብ ጉጅ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ፣ ኢታንግ፣ ኑዌር እና አኝዋክ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ቡርጅ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በኮራሪት፣ አሰገደ፣ ታህታይ አዲያቦ፣ ጭላ፣ ናእደር፣ አህፈሮመ፣ አዲአርቃይ፣ ደባርቅ፣ ጭልጋ፣ ቋራ፣ ደሀና፣ ባቲ፣ አርጎባ፣ ዳዋጨፋ፣ ተላላክ፣ ዳዌ፣ ኩነባ፣ አዳአር፣ ጉባ፣ ወንባራ፣ ጃውይ፣ ቡለን፣ ሸርኮል፣ ሰዳል፣ መዚንጋ፣ ጉቶጊዳ፣ ሳሲጋ፣ ጮቢ፣ ኢፋታ፣ በረህ፣ አሌልቱ፣ አዲስ አበባ፣ ወንጭ፣ ሶዶ፣ ቸሀ፣ እነሞር፣ ጌታ፣ ወልበርግ፣ ስልጤ፣ ዳሉቻ፣ ቡርሳ፣ ሊሙቢልቢሎ፣ ማሻ እና መንገሽ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, Weather conditions favorable to the formation of rain will intensify. In association with this, the central, northwest, southeast, south and east zones of Tigray region; from the Amhara region, north, west, south and central Gondar, west, north and east Gojjam, Awi, north and south Wollo, Oromo ethnic special zone, north Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, east, west, Kelem and Horogudru Wellega, west, southwest, east and north Shewa, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Bale and east Bale, Guji and west Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Benishangul Gumuz region: Asossa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones; from Gambella region: Majang, Itang, Nuer and Agnuwak zones; from Southwestern Ethiopia region: Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dawro zones; Central Ethiopia region: Gurage, Kebena Special zone, East Gurage, Mareko Special zone, Silte, Yem Special Zone, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; Sidama region zones; from Southern Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Gedio, Kore, Burji, south Omo and Basketo zones and from Afar region Ausi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones, from Somali region Siti and Fafen zones will receive light to moderate amount of rain in most areas. In addition, due to the intensifying weather events, there will be more than 30 mm of heavy rainfall in 24 hours in the areas of Korarit, Asegde, Tahtai Adiabo, Chila, Nadeer, Aheferom, Addarkay, Debark, Chilga, Quara, Dehana, Bati, Argoba, Dawachefa, Talalak, Dawe, Kuneba, Adaar, Guba, Wanbera, Jawi, Bullen, Sherkole, Sedale, Mezinga, Gutogida, Sasiga, Chobi, Ifata, Bereh, Aleltu, Addis Ababa, Wenchi, Sodo, Cheha, Enemor, Geta, Wolberg, Silte, Dalucha, Bursa, Limubilbilo, Masha and Mengeshi in 24 hours.