Daily Weather Report 25 September 05
Weather Summary for previous day
ባለፉት ሁለት ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በ10 የሚያህሉ ቦታዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
In the previous two days, there was cloud cover the Kiremt rain-benefiting areas of our country. In this regards, many places received light to moderate (1-29 mm) amount rainfall. Additionally, heavy rainfall exceeding 30mm within a 24-hour was recorded in approximately 10 places.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ፣ ሀሪ እና ቅልበቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በዳንግላ፣ ጓንጓ፣ ሸርኮል፣ ሳዮኖሌ፣ ኖሌካባ፣ ሳሲጋ፣ ሌካዱለቻ፣ አርጆ፣ ዳሪሙ፣ ጨዋቃ፣ መኮ፣ ደጋ፣ ሊሙሰቃ፣ ሊሙኮሳ፣ ጎማ፣ ሜና፣ ደዴሳ፣ ቦርቻ፣ ሰተማ፣ ሲግሞ፣ ሸቤሳምቦ፣ አደይዮ፣ ቱሉ፣ ቸታ፣ ዲሳ፣ ሎማ፣ ማሻ፣ ሻይቤንች፣ ጋችት፣ መንቲሻሻ፣ ኪንዶ ዳዳየ፣ ሶዶ ዙሪያ፣ ዳሞት ሶሮ፣ ቤንሳ፣ ጭሬ፣ ነንሴቦ፣ ራፔ እና ጩርሶ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, our forecast data indicates that the rain bring weather events will continue over the Kiremt rain benefiting areas of our country that rely on winter rainfall. In association with this, the Central, Northwest, Southeast, South, and East zones of the Tigray Region; North, West, South, and Central Gondar of the Amhara Region; West and East Gojjam; Awi; North and South Wollo; the Oromo Ethnic Special Zone; North Shewa and Waghemra Zones; the Oromia Region including Jimma, Ilubabor, Buno Dele, West, East, Kelem, and Horogudru Wolga; West, Southwest, East, and North Shewa; Arsi and West Arsi; West and East Hararge; Bale; Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Itang, Nuer, Agnwuak and Majang zones of the Gambella region; Assossa, Mao Como, Kamash and Mekelle zones of the Benishangul-Gumuz region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dauro zones from the Southwest Ethiopia region; from the Central Ethiopia Region including Gurage, East Gurage, Kebena Special Zone, Mareko Special Zone, Yem Special Zone, Silte, Halaba, Hadia, Kembata and Tembaro zones; Sidama Regional Zones; and from Southern Ethiopia the regions of Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Kore, Gardula, Ale, Burj, Konso, and Gedeo; the Gabi, Hari and Kilbeti zones of the Afar region and the Fafen zone of the Somali region will receive light to moderate amounts of rainfall at many of their places. Additionally, due to the intensifing weather events, Dangla, Guangua, Sherkole, Sayo Nole, Nole Kaba, Sasiga, Lekadulecha, Arjo, Darimu, Salta, Meko, Dega, Limuseka, Limukosa, Goma, Mena, Dedessa, Borcha, Satema, Sigmo, Shebesambo, Adeyio, Tulu, Cheta, Disa, Loma, Masha, Shaybench, Gacht, Mentishasha, Kindo Dadaye, Sodo Around, Damot Soro, Bensa, Tere, Nencebo, Rappe, and Churso will have heavy rainfall exceeding 30mm within a 24-hour.