Daily Weather Report 25 September 03
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በ8 የሚያህሉ ቦታዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the areas of our country that benefited from the kiremt rains had cloud cover and accumulation. In connection with this, many places received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, about 8 places recorded heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከጋምቤላ ክልል አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባሰኬቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ቡርጅ፣ ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የሀውሲ፣ ቅልበቲ፣ ጋቢ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ሽራሮ፣ ሽሬእንዳስላሴ፣ ታህታይ ማይጨው፣ ቆላ ተምቤን፣ አድዋ፣ ሀገረ ሰላም፣ ፍረወይኒ፣ ሀውዜን፣ በርሀሌ፣ አፍዴር፣ ባህርዳር ዙርያ፣ አዴት፣ ጊዳአያና፣ ሀሮ ሊሙ፣ አምቦ፣ ደንዲ፣ ጅባት፣ ሊበን ጃዊ፣ ወሊሶ፣ ወንጪ እና አመያበ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow Weather conditions that are conducive to the formation of kiremt rains will strengthen. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghemra zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, East, West, Kelem and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena, Bale and East Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; Agnuak and Majang zones from Gambella region; Asosa, Mao Komo, Kamash and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones from Southwestern Ethiopia region; The Central Ethiopian Region includes the Gurage, East Gurage, Mareko Special Zone, Yem Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones; the Sidama Region zones; the Southern Ethiopian Region includes the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Gardula, Kore, Ale, Burj, Konso, South Omo and Gedio zones; the Afar Region includes the Ausi, Kilbeti, Gabi, Hari and Fanti zones; and Siti and Fafen zones of the Somali region will experience light to moderate rainfall at many places. In addition, due to the strengthening weather events, Shiraro, Shireendesilase, Tahtai Maichew, Kola Temben, Adwa, Hagere Selam, Freweini, Hawzen, Berahale, Afder, Bahir Dar Zuriya, Adet, Gidayana, Haro Limu, Ambo, Dendi, Jibat, Liben Jawi, Woliso, Wenchi and Amaya will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours.