Daily Weather Report 25 September 02

Weather Summary for previous day

Sept. 1, 2025

በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአንገር ጉትን፣ አታንጎ፣ መተማ እና ደብረሲና በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the areas of our country that benefited from winter rain experienced cloudy skies and fog. Additionally, many locations recorded rainfall ranging from light to moderate amounts (1-29 mm). Furthermore, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours was reported in Anger Gutin, Atango, Metema and Debre Sina.

Weather Forecast for next day

Sept. 3, 2025

በነገው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ቄለምና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የኢታንግ፣ ኑዌር፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ ማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ፣ ፋንቲ፣ አውሲ፣ ቅልበቲ፣ ሀሪ እና ማሂ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ በፀሀይ ሀይል ታግዘው ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በታህታይ አዲያቦ፣ አዲዳሮ፣ አስገዲ፣ እንደፈላሲ፣ አድዋ፣ ጸለምት፣ በየዳ፣ ጠለምት፣ ጃናሞራ፣ ሳሃላ፣ አዋበል፣ ወረጃርሶ፣ ግንደበረት፣ ጀልዱ፣ ኮቢ፣ ኤጀሬ፣ ኢፋታ፣ ደንዲ፣ ባኮጢቤ፣ ጎቡሳዮ፣ ሲቡሲሬ እና ቦነያቦሽ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, there will be significant cloud cover and rain accumulation across the Kiremt rain-benefiting areas of our country. In association with this from the Tigray region Central, Northwest, Southeast, South, and East zones; from the Amhara region North, West, South, and Central Gondar, West and East Gojjam, Awi, North and South Wollo, special zones of the Oromo ethnic group, North Shewa, and Wag Hemra zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West, East, Kelem, and Horogudru Wellega, West, Southwest, East, and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Harerge, Bale, Guji, and West Guji zones; Addis Ababa; Dire Dawa; from Gambella region Itang, Nuer, Anoka, and Majang zones; from Benishangul Gumuz region Assosa, Mao Komo, Kamashi, and Metekel zones; from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kaffa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Central Ethiopia region Gurage, East Gurage, Kebena special zone, Mareko special zone, Me special zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata, and Tembaro zones; Sidama region zones; from South Ethiopia region Wolayta, Gamo, Gofa, Basketo, Gardolla, Kore and Gedeo zones; from Afar region Gabi, Hari, Awusi, Fanti, Kilbeti and Mahi zones; and from Somali region City and Fafen zones will receive light to moderate amount of rainfall. Additionally, due to weather events that are enhanced by occasional solar energy, the areas of Tahtai Adiabo, Adidaro, Asgedi, Falasi, Adwa, Tselem, Yeda, Tselem, Janamora, Sahala, Awabel, Werejarso, Gdebret, Jeldu, Kobi, Ejere, Ifata, Dundee, Bakotibe, Gobusayo, Sibusire, and Bonyabosh are expected to experience heavy rainfall exceeding 30mm within a 24-hour.