Daily Weather Report 25 September 01
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በ11 በሚያህሉ አካባቢዎች ላይ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the areas of our country that benefited from the Kiremt rains had cloud cover. In connection with this, many areas received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, 11 areas recorded heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለክረምት ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በተመሳሳይ ገጽታ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ፣ ቦረና ፣ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማኦ ኮሞ፣ ካማሽ እና መተከል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጋርዱላ፣ ቡርጅ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ እና ሀሪ ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአቢይአዲ፣ እብናት፣ አዲስ ዘመን፣ ቡግና፣ ወረታ፣ ፎገራ፣ ወግዲ፣ ወንበራ፣ እናርጅ እናውጋ፣ ደጀን፣ ደምበጫ፣ ጊዳአያና፣ ሊሙ፣ ነቀምቴ፣ ኢልፋታ፣ አምቦ፣ ወሊሶ፣ ቸሃ፣ ሊሙ ሰቃ፣ ሊሙ ኮሳ፣ ቀርሳ፣ ወልበርግ፣ ወንጪ፣ አቃቂ እና አዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow Weather conditions that are conducive to the formation of Kiremt rains will continue in the same pattern. In this regard, the Central, Northwest, Southeast, South and East zones of Tigray Region; From the Amhara region, North, West, South and Central Gondar, West and East Gojam, Awi, North and South Wollo, Oromo National Special Zone, North Shewa and Waghema zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West, East and Horogudru Wollega, West, South West, East and North Shewa, Arsi and West Arsi, West and East Hararge, Borena, Bale and East Bale, Guji and West Guji zones; Addis Ababa; Anuak and Majang zones from Gambella region; Mao Komo, Kamash and Metekel zones from Benishangul Gumuz region; Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, East Gurage, Marekko Special Zone, Yem Special Zone, Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tembaro zones from Central Ethiopia region; Sidama Region zones, Wolaita, Gamo, Gofa, Gardula, Burj and Gedio zones of Southern Ethiopia Region; Gabi and Hari zones of Afar Region will receive light to moderate rainfall at many places. Also, Abiyadi, Ebnat, Addis Zemen, Bugna, Wereta, Fogera, Wagdi, Wenbera, Enarj and Awga, Dejen, Dembecha, Gidaayana, Limu, Nekemte, Ifata, Ambo, Wolisso, Chacha, Limu Seka, Limu Kosa, Kersa, Wolberg, Wenchi, Akaki and Addis Ababa will experience heavy rainfall of more than 30mm within 24 hours.