Daily Weather Report 25 October 31

Weather Summary for previous day

Oct. 30, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጎንደር፣ ሻሁራ፣ አሶሳ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ጨዋቃ፣ ጋምቤላ፣ አማን፣ ማጂ፣ አርባምንጭ፣ ዲላ፣ አሺ፣ ጉበቲ፣ ኩሚ፣ ሙጊ፣ ሲቦ እና መንደር 11 ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በአቦቦ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the south and southeast, as well as the west and southwest regions of the country, which are in their second rainy season of the bega. In this regard, in Gondar, Shahura, Asosa, Nejo, Aira, Gimbi, Chewaka, Gambella, Aman, Maji, Arbaminch, Dilla, Ashi, Gubeti, Kumi, Mugi, Sibo and Village 11 received light to moderate (1-29mm) rainfall, while Abobo received heavy rainfall. On the other hand, the northern, central, northeastern and eastern parts of the country experienced dry, sunny and windy bega weather. Additionally, the lowest temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius

Weather Forecast for next day

Nov. 1, 2025

በነገዉ ዕለት ለበጋ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይጠናከራሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ሸበሌ፣ አፍዴር፣ ዳዋ፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ እና ኤረር ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሚ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የጅማ፤ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች፤ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ የአኝዋክና ማጃንግ ዞኖች፤ የማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር እና ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በማሻ፣ የኪ፣ ቴፒ እና ሸኮ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ በጥቂት የምስራቅ አማራ አከባቢዎች የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ10 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow Weather conditions that are conducive to the occurrence of bega rains will intensify in the southern and southeastern regions of our country. In this regard, the Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedio zones of the Southern Ethiopia Region; All zones of Sidama Region; Liben, Shebele, Afder, Dawa, Korahe, Nogob and Erer zones of Somali Region; West Arsi, Bale and East Bale zones of Oromia Region; Guji and West Guji, Borena and East Borena zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. In addition, Jimma; Ilubabor, Kelem Wellega, East and West Hararge; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Hadiya, Halaba, Yem liyu Zone, Kembata and Tembaro zones; Anwak and Majang zones; Central and West Gondar and West and East Gojjam zones will receive light to moderate rainfall at some places. In addition, based on the intensifying weather events, Masha, Yeki, Tape and Sheko will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, dry, sunny and windy bega weather will be observed in the northeast, central and eastern parts of the country; Forecast data indicates that the daily minimum temperature will be recorded below 10 degrees Celsius in some areas of Eastern Amhara.