Daily Weather Report 25 October 30

Weather Summary for previous day

Oct. 29, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደባርቅ፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ ፓዊ፣ ነጆ፣ አይራ፣ ዶሎመና፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ቡሬ፣ ማሻ፣ ቴፒ፣ አማን፣ ማጂ፣ ሳውላ፣ ምዕራብ አባያ፣ አርባምንጭ፣ ቦሬ ቡርጂ፣ ያቤሎ፣ ሞያሌ፣ ፉጎሌቃ፣ አሺ፣ ጌቻ፣ ቅዳሜ ገበያ፣ ኦቦመሪጋ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በጂንካ እና መንደር 7 ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the south and southeast as well as the west and southwest regions of the country, which are in their second rainy season of the bega. In this regard, in Debark, Dangla, Chagni, Pawe, Nejo, Aira, Dolomena, Gambella, Fuengdo, Bure, Masha, Tepi, Aman, Maji, Saula, West Abaya, Arbaminch, Bore Burji, Yabelo, Moyale, Fugoleka, Ashi, Gecha, Kidame Gbeya, Obomeriga received light to moderate (1-29mm) rainfall, while Jinka and Village 7 received heavy rainfall. On the other hand, the northern, central, northeastern and eastern regions of the country have experienced dry, sunny and windy bega weather. In addition, the daily minimum temperature has been recorded below 5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

Oct. 31, 2025

በነገዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ሸበሌ፣ አፍዴር፣ ዳዋ፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ እና ኤረር ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሚ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የጅማ፤ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች፤ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ የአኝዋክና ማጃንግ ዞኖች፤ የማዕከላዊ ጎንደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ በጥቂት የምስራቅ አማራ አከባቢዎች የቀኑ ዝቀተኛ የሙቀት መጠን ከ10 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች እንደሚሆን አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the southern and southeastern regions of our country, which are in their second rainy season of the bega. In this regard, in the Southern Ethiopia Region, Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedio zones; All Sidama Region zones; Somali Region Liben, Shebele, Afder, Dawa, Korahe, Nogob and Erer zones; Oromia Region West Arsi, Bale and East Bale; Guji and West Guji, Borena and East Borena zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Also, Jimma; Ilubabor, Kelem Wellega, East and West Hararge; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones; Anwak and Majang zones; Central Gondar and West Gojam zones will receive light to moderate rainfall in some areas. On the other hand, dry, sunny, and windy bega weather is expected in the northeast, central, and eastern parts of the country; numerical forecast indicate that the daily minimum temperature will be below 10 degrees Celsius in some areas of eastern Amhara.