Daily Weather Report 25 October 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ ኦሮሚያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ በሌላ በኩልም ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ምዕራብ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ምዕራብ አማራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቡለሆራ፣ ነገሌ፣ ቦሬ፣ ኮንሶ፣ ጂንካ፣ ማጂ፣ ዲላ፣ አሶሳ፣ ማንኩሽ፣ ጋምቤላ፣ አሺ፣ ጉበቲ፣ ቅዳሜገበያ፣ ትንሹሜጢ፣ ጌጫ፣ ነጆ፣ ጊምቢ፣ ጊዳአያና፣ ነቀምቴ፣ ቡሬ፣ ጎሬ፣ መቱ፣ ቢላምቢሎ፣ ፉጎሌቃ፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ መካነ ኢየሱስ፣ ጎንደር እና ደብረታቦር ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡
Yesterday, south Oromia and south Ethiopia, which are in their second rainy season of the Bega, had cloud coverage. On the other hand, Benshangul Gumuz, Gambella, west Oromia, southwest Ethiopia, and west Amhara had cloud coverage. In this regard, Bulehora, Negelle, Bore, Konso, Jinka, Maji, Dilla, Asossa, Mankush, Gambella, Ashi, Gubeti, Kidame Gebeya, Tinishu Meti, Gecha, Nedjo, Gimbi, Gidayana, Nekemte, Bure, Gore, Mettu, Bilambilo, Fugoleka, Dangila, Chagni, Mekane Yesus, Gondar, and Debretabor received light to moderate rain. In contrast, the northeast, central, and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደማና ሽፋን በመነሳት በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ በጥቂት የምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ በጥቂት የሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የሳለኖኖ፣ ማሻ፣ የኪ፣ ገሻ፣ ደቻ፣ ቱሎ፣ ዲሳ፣ ባስኬቶ እና አሌ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ይስተዋልባቸዋል፡፡
For the coming day, the south and southeast parts of our country, which are in their second rainy season of the Bega, will have cloud coverage. In this respect, from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, west Arsi, Bale and east Bale; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedeo; zones of the Sidama region, and from the Somali region Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Jarar and Erer zones will receive light to moderate (1-29 mm) rain. Moreover, due to the prevailing cloud coverage, Jimma, Ilubabor, Kelam Wellega, a few zones of west and east Hararge zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro, and Konta zones; Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; Majang and Agnuak zones; and a few areas of north and south Gondar zones will experience light to moderate rainfall. Additionally, a few areas of Salenono, Masha, Yeki, Gesha, Decha, Tullo, Disa, Basketo, and Ale will experience heavy rain within 24 hours due to the severe weather events. Conversely, dry, sunny, and windy Bega weather will prevail in the northeastern, central, and eastern parts of the country.