Daily Weather Report 25 October 28
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አይከል፣ ሻሁራ፣ ባህርዳር፣ ዳንግላ፣ ሞጣ፣ ላይበር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ጋምቤላ፣ ዶሎመና፣ ጎሬ፣ ጊምቢ፣ ጊዳአያና፣ ነቀምቴ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ ሊሙገነት፣ ጅማ፣ ጂንካ፣ ማሻ፣ አማን፣ ምዕራብ አባያ፣ ቡርጂ፣ ዲላ፣ ቦሬ፣ ገለምሶ፣ ሲቦ፣ አሺ፣ ቀብሪደሃር፣ ኩሚ፣ ወልቂጤ፣ ይርጋለም፣ አጋሮ፣ ቢላምቢሎ፣ ፉጎሌቃ፣ መቱ፣ ያንፋ እና ያዮ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡
Yesterday, there was a cloud cover over the south and southeast as well as the west and southwest regions of the country, which are in their second rainy season of the bega. In this regard, Ayikel, Shahura, Bahir Dar, Dangla, Mota, Liber, Debre Markos, Gambella, Dolo mena, Gore, Gimbi, Gidayana, Nekemte, Arjo, Bedele, Limugenet, Jimma, Jinka, Masha, Aman, West Abaya, Burji, Dilla, Bore, Gelemso, Sibo, Ashi, Kebridehar, Kumi, Welkite, Yirgalem, Agaro, Bilambilo, Fugoleka, Metu, Yanfa and Yayo received light to moderate (1-29mm) rainfall. On the other hand, the northern, central, northeastern, and eastern regions of the country have experienced dry, sunny, and windy summer weather.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት ለበጋ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስከቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ሸበሌ፣ አፍዴር፣ ዳዋ፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ እና ኤረር ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሚ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፤ በደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም የጅማ፤ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ የአኝዋክ፣ ኢታንግና ማጃንግ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በማሻ፣ ሳውላ፣ ገዜ ጎፋ፣ ቦና ዙርያ እና ጎሮ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡
Tomorrow Weather conditions that are conducive to the occurrence of bega rains will continue to strengthen in the southern and southeastern regions of our country. In this regard, the following zones of the Southern Ethiopia Region are affected: Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedio; all zones of the Sidama Region; Liben, Shebele, Afder, Dawa, Korahe, Nogob and Erer zones of Somali region; West Arsi, Bale and East Bale zones of Oromia region; Guji and West Guji, Borena and East Borena zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. On the other hand, there will be cloud cover over the western, southwestern and central parts of the country. Therefore, Jimma; Ilubabor, Buno Bedele, Horo Gudru, Kelem, West and East Wellega, North, Southwest and West Shewa, East and West Hararge, Arsi; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Gurage, East Gurage, Silte, Kebena Special Zone, Marekko Special Zone, Hadiya, Halaba, M' Special Zone, Kembata and Tembaro Zones; Anwak, Itang and Majang Zones; North, South and Central Gondar, West and East Gojam will experience light to moderate rainfall. In addition, based on the strengthening weather events, Masha, Saula, Geze Gofa, Bona Zuria and Goro will receive heavy rainfall of more than 30 mm in 24 hours. On the other hand, the northeastern parts of the country will experience dry, sunny and windy bega weather.