Daily Weather Report 25 October 27

Weather Summary for previous day

Oct. 26, 2025

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ኮንሶ፣ ጂንካ፣ አርባ ምንጭ፣ ቀብሪዳሃር፣ ጊዳአያና፣ ቻግኒ፣ ዳንግላ፣ በማንኩሽ፣ አሺ፣ ትንሹ ሜጢ፣ ቢላምቢሎ እና ፉጎሌቃ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over the south and southeast parts of the country, which are in their second rainy season of the Bega, as well as the western and southwestern parts of the country. Along with this, Moyale, Yabelo, Konso, Jinka, Arba Minch, Kebridahar, Gidayana, Chagni, Dangila, Mankush, Ashi, Tinishu Meti, Bilambilo, and Fugoleka received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Conversely, the northeastern, central, and eastern parts of the country experienced dry, sunn,y and windy Bega weather.

Weather Forecast for next day

Oct. 28, 2025

በነገው ዕለት ለበጋ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ዶሎ፣ ኖጎብ እና ኤረር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለምና ምዕራብ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ የደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የማሻ፣ ገሻ፣ ማጂ፣ ሱርማ፣ ገና፣ ኦሞ በያም፣ ክንዶ ዲዳዬ፣ ካዎ ኮይሻ፣ ቁጫ፣ አሮሬሳ፣ ቡራ፣ ቦናዙሪያ፣ ሀረና ቡሉቅ፣ ኦቦርሶ እና ሞያሌ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

For the coming day, weather events favorable to the formation of Bega rain will be more intense in the southern and southeastern parts of our country, which are in their second rainy season of Bega. In this respect, from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, west Arsi, Bale and east Bale zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedeo zones; Sidama region zones, and from the Somali region Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Korahe, Dollo, Nogob and Erer zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. On the other hand, cloud coverage is expected over the western, southwestern, central, northeastern, and eastern areas of the country. Hence, the zones of Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horro Guduru, Kelam and west Wellega, north, west and south west Shewa, Arsi, west and east Hararge; the zones of Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro and Konta; the zones of Gurage, Silte, Kebena special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro; the zones of Majang and Agnuwak; the zones of south Gondar, east Gojjam, Waghemra, north and south Wollo and the zones of central, east, south and south east Tigray region will have rain. Moreover, based on the occasional strengthening weather phenomena, a few areas of Masha, Gesha, Maji, Surma, Gena, Omo Beyam, Kindo Diddaye, Kawo Koisha, Kucha, Aroresa, Bura, Bonazuria, Harena Buluk, Oborso, and Moyale will experience heavy rainfall within 24 hours.