Daily Weather Report 25 October 26
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሲዳማ ፣በደቡብ ኦሮሚያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ እንዲሁም በጋምቤላ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ እና በምዕራብ አማራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጥቂት ቦታዎቻቸው ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡በተጨማሪም በጎሬ 31.9 ሚ.ሜ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡
Yesterday there were cloudy conditions within Sidama, South Oromia and Southern Ethiopia, as well as in Gambela, West Oromia and West Amhara. In some of these places light to moderate rainfall (1–29 mm) was recorded. Additionally, in Gore 31.9 mm of heavy rain was recorded within 24 hours, exceeding 30 mm. On the other hand, in the northeastern, central and eastern parts of the country the Bega weather was dry, sunny and windy.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ኖጎብ፣ ኤረር እና ዶሎ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በጥቂት የሰሜንና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ የምዕራብ ሸዋ፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማኦኮሞ እና አሶሳ ዞኖች፤ የማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የደቡብ ጎንደር፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡
Tomorrow, during the day, a second wet spell will bring cloudy conditions to parts of our country in the south and southeast. In addition, rain with amounts ranging from light to moderate (1–29 mm) is expected in the following zones: From Oromia Guji and West Guji, Bale and East Bale, Arsi and West Arsi, Borena and East Borena; From Southern Ethiopia Region Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedeo; From Somali Region Dawa, Liben, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Erer and Dolo; and in the zones of Sidama. Additionally, cloudy conditions are expected over western, southwestern and some northern and northeastern parts of the country. Consequently, light rain is forecast for these areas: Jimma, Iluababora, Buno Bedele, West Shewa, Kellem and West Wollega zones; Bench Sheko, Sheka, Kefach, Dawuro and Konta zones; Gurage, East Gurage, Kibena special zone, Mareko special zone, Mu special zone,Silte, Halaba, Hadiya, Kembata and Tambaro zones; Mao komo and Asosa zones; Central, Southeastern, Southern and Eastern Tigray zones; South Gondar, East Gojjam, North and South Wollo and Wag Hemra zones; and the Agnuak and Majang zones, where some locations will see light precipitation. Elsewhere, the northern, northeastern, central and eastern parts of the country will experience the typical Bega weather of dry, sunny and windy conditions.