Daily Weather Report 25 October 25

Weather Summary for previous day

Oct. 24, 2025

በትናንትናው ዕለት በሲዳማ እና በደቡብ ኢትዮጵያ እንዲሁም በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና በምዕራብ አማራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡

Yesterday, there were cloudy conditions in Sidama region and Southern Ethiopia region, as well as in Western Oromia, Benishangul-Gumuz and Western Amhara. In some of those places, received light rain. Meanwhile, in the northern, northeastern, central and eastern parts of the country, the weather was dry, sunny and windy.

Weather Forecast for next day

Oct. 26, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌና ምስራቅ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በጥቂት የሰሜንና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ የምዕራብ ሸዋ፣ ቄለም፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማኦኮሞ፣ መተከል እና አሶሳ ዞኖች፤ ማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ፣ ሰሜን ወሎ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡

Tomorrow, the south and south east parts of our country, which are in their second rainy season which is Bega, will have cloud coverage. In line with this, From Oromia: Guji and West Guji, Bale and East Bale, West Arsi, Borena and East Borena zones; From South Ethiopia Region: Wolayita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedeo zones and in the Sidama region will receive light rain. In addition to this, in western, southwestern, and some northern and northeastern parts of the country there will be cloud coverage. As a result, light rain is expected in the following zones: Jimma, Illubabor, Buno Bedele, West Shewa, Kellem, West and East Wollega; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Dawuro and Konta; Hadiya, Halaba, the special zone of Yem, Kembata and Tambaro; Ma’o komo, Metekel and Asosa; Central, Southeastern, Southern and Eastern Tigray zones; Southern Gondar, West and East Gojjam, Awi zone, North Wollo and Wag Hemra; and the Agnuak and Majang zones, will receive light rain. Elsewhere, in the northeastern, central and eastern parts of the country, the weather will be dry, sunny and windy during the daytime.