Daily Weather Report 25 October 24

Weather Summary for previous day

Oct. 23, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ ኦሮሚያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ እንዲሁም በጋምቤላ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና በምዕራብ አማራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቦረካ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡

Yesterday, there was a cloud cover in southern Oromia and southern Ethiopia, as well as Gambella, western Oromia, southwestern Ethiopia, Benshangul-Gumuz, and western Amhara. In this regard light to moderate rainfall (1-29 mm) were received in a few places. Additionally, more than 30 mm of heavy rainfell were recorded in Boreka. Conversely, the northeast, central, and eastern regions of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather conditions.

Weather Forecast for next day

Oct. 25, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በጥቂት የሰሜን ምዕራብና ሰሜንምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ የምዕራብ ሸዋ፣ ቄለም፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማኦኮሞ፣ መተከል፣ ካማሽ እና አሶሳ ዞኖች፤ የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የደቡብ ጎንደር፣ አዊ እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች እና የምስራቅና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡

For the coming day, the south and south east parts of our country, which are in their second rainy season of Bega, will have cloud coverage. Along with this, from Oromia region Guji and west Guji, Bale, west Arsi, Borena, and east Borena zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji, and Gedeo zones, and the Sidama region zones will receive light rain. Besides, there will be cloud coverage and accumulation over the western, southwestern, and a few places of northwestern and northeastern parts of the country. Accordingly, in Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, west Shewa zone, Kelam, west and east Wellega zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Dawuro and Konta zones; Hadiya, Halaba, Yem especial zone, Kembata and Tembaro zones; Mao Komo, Metekel, Kamashi and Asossa zones; Agnuak and Majang zones; south Gondar, Awi and west Gojjam zones and east and central Tigray zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in some places. Conversely, the dry, sunny, and windy weather of the Bega season will prevail over the north-eastern, central, and eastern portions of the country.