Daily Weather Report 25 October 23

Weather Summary for previous day

Oct. 22, 2025

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፣ ደቡብ ኦሮሚያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ በሌላ በኩልም ጋምቤላ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጠንካራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቅዳሜገበያ፣ ኦቦመርጋ፣ ጨዋቃ፣ ቢላምቢሎ እና በቡሬ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡

Yesterday, the southern parts of the Somali region, south Oromia, and southern Ethiopia, which are in their second rainy season of the Bega, on the other hand, Gambella, west Oromia, and southwestern Ethiopia had strong cloud coverage. In association with this, some places received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Moreover, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Kidame Gebeye, Obbo Merga, Cheweka, Bilambilo, and Bure. In contrast, the northeast, central, and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather.

Weather Forecast for next day

Oct. 24, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎችም ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ በጥቂት የምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማኦኮሞ፣ መተከል፣ ካማሽ እና አሶሳ ዞኖች፤ የአኙዋክ እና ኑዌር ዞኖች፤ የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡

For the coming day, the south and south east parts of our country, which are in their second rainy season of Bega, will have cloud coverage. Along with this, from Oromia region Guji and west Guji, west Arsi, Borena, and east Borena zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji, and Gedeo zones, and the Sidama region zones will receive light rain. Besides, there will be cloud coverage and accumulation over the northwestern, western, and southwestern parts of the country. Thus, the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, some parts of the west Shewa zone, Horro Guduru, Kelam, west and east Wellega zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro and Konta zones; Hadiya, Yem especial zone, Kembata and Tembaro zones; Mao Komo, Metekel, Kamashi and Asossa zones; Agnuak and Nuwer zones; north, west, south and central Gondar, Awi none, north and west Gojjam zones will experience light to moderate rainfall (1-29 mm) at some places. Conversely, the dry, sunny, and windy weather of the Bega season will prevail over the north-eastern, central, and eastern portions of the country.