Daily Weather Report 25 October 21

Weather Summary for previous day

Oct. 20, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛውና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጋምቤላ፣ ትንሹሚጢ፣ ፓዌ፣ አርጆ፣ ካችሴ፣ አጋሮ፣ ያንፋ፣ ተርጫ እና አርባምንጭ 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was significant cloud cover and accumulation in south and southeast parts of our country which are in their second rainy season of the Bega as well as western half, central, and northeastern parts of our country. In this regards, Light to moderate rainfall (1-29 mm) was recorded in many areas. Additionally, more than 30 mm of heavy rain fell within 24 hours were recorded in Gambella, Tineshumetti, Pawe, Arjo, Kachise, Agaro, Yanfa, Tercha, and Arbaminch.

Weather Forecast for next day

Oct. 22, 2025

በነገው ዕለት ዝናብ ሰጭ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የቆራሔ እና ዶሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ አጋማሽ፣ መካከለኛው እና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፤ አዲስ አበባ፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የአሶሳ፣ መተከል እና ካማሽ ዞኖች፤ የማጃንግ፣ አኙዋክ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሰሜን ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ የሰሜንምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች እና ከአፋር ክልል የቅልበቲ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በወንበራ፣ ሰዳል፣ ሸርኮሌ፣ ኩርሙክ፣ አሶሳ፣ ማኦኮሞ፣ ጊዳሚ፣ አንፊሎ፣ ሳዮ፣ ሳዲጨንቃ፣ ቤጊ፣ ቡሬ፣ ያዩ፣ ጅማ አርጆ፣ ጅማ ራሬ፣ ሜና፣ ሳይለመ፣ ጌሻ፣ ማሻ፣ ጊቤ፣ ጎምቦራ፣ ጠምባሮ፣ ጌና፣ ቦሎሶቦምቤ እና ጎርጨ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡

Tomorrow, rain-bearing weather systems are expected to persist over the south and southeast parts of our country which are in their second rainy season of the Bega. In connection with this, areas in the Oromia region including Guji, west Guji, Borena, east Borena, west Arsi, Bale, and east Bale zones; Southern Ethiopia region such as Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji, and Gedio zones, the Sidama region zones; and from Somali region Korahe and Doolo zones, are expected to receive light to moderate (1 to 29 mm) rainfall. Meanwhile, in western half, central, and northeastern parts of the country are likely to experience cloud cover and accumulation. Accordingly, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru Kelem, west and east Wellega, north, west, southwest, and east Shewa, Arsi; Addis Ababa; Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro, and Konta zones; Gurage, Silte, Kebena special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata, and Tembaro zones; Asosa, Metekel, and Kamashi zones; Majang, Anuak, Nuer, and Itang zones; north, west, south, and central Gondar, Awi zone, west, east, and north Gojjam, Waghemra, north and south Wollo; northwest, east, south, and southeast Tigray; and e Kilbeti zone of Afar region are also expected to receive light to moderate rainfall. Additionally, due to the strengthening of certain weather systems, heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours is likely to occur in Wanbera, Sedal, Sherkole, Kurmuk, Asosa, Mao Komo, Gidami, Anfilo, Sayo, Sadi Chanka, Begi, Bure, Yayu, Jimma Arjo, Jimma Rare, Mana, Sailem, Gecha, Masha, Gibe, Gombora, Tembaro, Gena, Boloso Bombe, and Gorche. On the other hand, the eastern parts of the country will continue to experience dry, sunny, and windy weather conditions.