Daily Weather Report 25 October 20

Weather Summary for previous day

Oct. 19, 2025

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በማጂ፣ ምዕራብ አባያ እና ያንፋ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over parts of the country, which are in their second rainy season of Bega, as well as the north, west, southwest, and central areas. Along with this, some areas received light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Maji, West Abaya, and Yanfa.

Weather Forecast for next day

Oct. 21, 2025

በነገው ዕለት ለበጋ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የቆራሔ፣ ዶሎ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ አጋማሽ፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማኦኮሞ፣ አሶሳ፣ መተከል እና ካማሽ ዞኖች፤ የማጃንግ፣ አኙዋክ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞኖች እና ከአፋር ክልል የቅልበቲ እና ፋንቲ ዞኖች ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጉባ፣ ዳንጉር፣ ቡለን፣ ፓዌ፣ ወንበራ፣ ሸርኮሌ፣ ኩርሙክ፣ አሶሳ፣ ካማሽ፣ ዳንግላ፣ ጊዳሚ፣ አንፊሎ፣ ሳዮ፣ ሳዲጨንቃ፣ ቤጊ፣ ጉቶጊዳ፣ ሳሲጋ፣ ዋዩቱቃ፣ ጅማ አርጆ፣ ቦነያ ቦሼ፣ ሲቡሲሬ፣ ጅማራሬ፣ ያዩ፣ አልጌ፣ በደሌ፣ ሰጠማ፣ ማጂ፣ መኒት ሻሻ፣ ባስኬቶ፣ አንጋጫ፣ ለሞ፣ ወራ፣ ጎርጬ፣ አርቤጎና እና ኮኮሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

For the next day, weather conditions favourable to the formation of Bega rain will continue over the south and southeast parts of our country, which are in their second rainy season of Bega. In this respect, from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, west Arsi, Bale and east Bale zones; from south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedeo zones; Sidama region zones, and from the Somali region Korahe, Dollo, Jarar and Erer zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall. Conversely, there will be strong cloud coverage and accumulation over the western half, central, north eastern, and eastern areas of the country. Thus, the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horro Guduru, Kelam, west and east Wellega, north, west, south west and east Shewa, Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro and Konta zones; Gurage, Silte, Kebena special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; Mao Komo, Asossa, Metekel and Kamashi zones; Majang, Agnuak, Nuwer and Itang zones; north, west, south and central Gondar, Awi zone, north, west and east Gojjam, Waghemra, north and south Wollo zones; central, east, south and south east Tigray zones and Kilbeti and Fanti zones of Afar region will rainfall. Moreover, based on the intensifying weather events, Guba, Dangur, Bulen, Pawe, Wenbera, Sherkole, Kurmuk, Asosa, Kamash, Dangila, Gidami, Anfilo, Sayo, Sadi Chenka, Begi, Gutogida, Sasiga, Wayu Tuka, Jimma Arjo, Boneya Boshe, Sibu Sire, Jimma Rare, Yayu, Alge, Bedele, Maji, Menit Shasha, Basketo, Angacha, Lemmo, Warra, Gorche, Arbegona, and Kokosa will experience heavy rainfall within 24 hours.