Daily Weather Report 25 October 18

Weather Summary for previous day

Oct. 17, 2025

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን፤ በሊሙገነት ደግሞ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ተስተዉሎባቸዋል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over parts of the country, which are in their second rainy season of Bega. In connection with this, some areas received light to moderate (1-29 mm) rainfall, while heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Limugenet. On the other hand, dry, sunny, and windy Bega weather prevailed in the northeastern, central, and eastern areas of the country.

Weather Forecast for next day

Oct. 19, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የቆራሔ፣ ሸበሌ፣ ዶሎ፣ ጃራር እና ኤረር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎችም ላይ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ በጥቂት የምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማኦኮሞ እና አሶሳ ዞኖች፤ የማጃንግ፣ አኙዋክ፣ ኑዌር እና ኢታንግ ዞኖች እና አዊ ዞን በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የኦሞ በያም፣ ማንቾ፣ ኦሞ ናዳ፣ ዋንታዎ፣ ጆሬ፣ ማሻ፣ የኪ፣ ጉራፈርዳ፣ ሸኮ፣ ቤንች፣ ገሻ፣ ቸና፣ ሺሾአንደ፣ ገዋታ፣ ጊምቦ፣ ኮንታ ኮይሻ፣ ጭዳ፣ ተርጫ፣ ሎማ፣ ዲሳ፣ ባስኬቶ፣ መሎኮዛ እና ገዜ ጎፋ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡

For the coming day, the south and south east parts of our country, which are in their second rainy season of Bega, will have cloud coverage. Along with this, from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, west Arsi, Bale and east Bale zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedeo zones; Sidama region zones and from Somali region Korahe, Shebelle, Dollo, Jarar and Erer zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall. Similarly, there will be cloud coverage over the western, southwestern, northwestern and eastern parts of the country. Thus, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horro Guduru, Kelam, west and east Wellega, few parts of west and southwest Shewa, Arsi, west and east Hararge zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro and Konta zones; Gurage, Silte, Kebena special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; Mao Komo and Asossa zones; Majang, Agnuak, Nuwer and Itang zones and Awi zone will receive light rain at some places. Besides, based on the occasional strengthening weather events, few areas of Omo Beyam, Mancho, Omo Nada, Wantawo, Jore, Masha, Yeki, Guraferda, Sheko, Bench, Gesha, Chena, Shisho Ande, Gewata, Gimbo, Konta Koisha, Chida, Tercha, Loma, Disa, Basketo, Melokoza and Geze Gofa will experience heavy rainfall within 24 hours. Conversely, the central and northeastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather.