Daily Weather Report 25 October 17

Weather Summary for previous day

Oct. 16, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአንዳንድ ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በማሻ፣ ቦሬ እና ቡሌሆራ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡

Yesterday, there was a cloud cover and accumulation over the southern and southeastern regions of the country, which are in the second rainy season of Bega, as well as the northwest, west, and southwest regions of the country. In these areas, light to moderate rainfall (1-29 mm) was reported in some locations. Additionally, more than 30 mm of heavy rainfall fell in Masha, Bore, and Bulehora within 24 hours. Meanwhile, dry, sunny, and windy Bega weather conditions were observed in the northern, northeastern, central, and eastern parts of the country.

Weather Forecast for next day

Oct. 18, 2025

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች ላይ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩልም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማኦኮሞ፣ መተከል፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ የማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የደዴሳ፣ ያዩ፣ ሳለኖኖ፣ ጮራ፣ ሰተማ፣ ሲግሞ፣ ጎማ፣ መልኮዛ፣ መሎጎዳ፣ ወነሶሾ እና ጋልሃሙር በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በመካከለኛው፣ በምስራቅ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡

For tomorrow Weather conditions conducive to the formation of bega rains will continue to strengthen in the southern and southeastern regions of our country, which are in their second rainy season of the Bega. In this regard, from Southern Ethiopian region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedio zones; all zones of Sidama region; from Somali region Liben, Shebele, Korahe, Nogob, Fafen, Jarar, Doolo and Erer zones; from Oromia region west Arsi, Bale and east Bale; Guji and west Guji, Borena and east Borena zones of the will receive light to moderate (1-29 mm) amount of rainfall at many places. On the other hand, there will be cloud cover and accumulation over the western, and southwestern parts of the country. In line with this, in Jimma; Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, West and East Wellega, Southwest and west Shewa and east Hararge zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Gurage, East Gurage, Silte, Kebena Special Zone, Mareko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tanbaro zones; Agniwak, Nuer, Itang and Majang zones zones; Asossa, Metekel, Kamash and Maokomo zones; west and East Gojam, Awi zone will experience light to moderate rain. Additionally, based on the intensifying weather events, Some areas in Dedessa, Yayu, Saleno, Chora, Setema, Sigmo, Goma, Melkoza, Melogoda, Wansosho, and Galhamur will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, the north eastern parts of the country will experience dry, sunny and windy Bega weather conditions.