Daily Weather Report 25 October 16
Weather Summary for previous day
በነገዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ተጠናክሮ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስከቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ ሁሉም የሲዳም ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ፣ ኖገብ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ዶሎና ኤረር ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ(1-29 ሚ.ሚ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም የጅማ፤ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ አርሲ፤ አዲስ አበባ፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግና ማጃንግ ዞኖች፤ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽና ማኦኮሞ ዞኖች፤ የሰሜን፣ ምዕራብ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጅማ ሆሮ፣ ጨዋቃ፣ ዋዩ ቱቃ፣ ጉቶ ጊዳ፣ ድጋ፣ ያዩ፣ አለ፣ ሸቤ ሳንቦ፣ ሎማ፣ ሀና ሶራ፣ አርዳ ጅሌ፣ አዶላ፣ በርበሬ እና ሁራጋ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡
For Tomorrow rainy weather events will continue to intensify in the southern and southeastern regions of our country, which are in their second rainy season of the Bega. In this regard, Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedio zones of the Southern Ethiopian Region; all zones of Sidama Region; Liben, Shebele, Korahe, Nogob, Fafen, Jarar, Dolo and Erer zones of the Somali Region; West Arsi, Bale and East Bale; Guji and West Guji, Borena and East Borena zones of the Oromia Region will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. On the other hand, there will be heavy cloud cover and accumulation over the western, southwestern, central and eastern regions of the country. Therefore, Jimma; Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, West and East Wellega, North, South West and West Shewa, East and West Hararge, Arsi; Addis Ababa; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Gurage, East Gurage, Silte, Kebena Special Zone, Mareko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tanbaro zones; Agniwak, Nuer, Itang and Majang zones; Asossa, Metekel, Kemash and Maokomo zones; North, West South and Central Gondar, North, West and East Gojam, Awi zone will experience light to moderate rain. Additionally, based on the intensifying weather events, Jimma Horo, Chewaka, Wayu Tuqa, Guto Gida, Dega, Yayu, Ale, Shebe Sanbo, Loma, Hana Sora, Arda Jile, Adola, Berbere and Huraga will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours. On the other hand, the north eastern parts of the country will experience dry, sunny and windy Bega weather conditions.
Weather Forecast for next day
በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ፣ በመካከለኛ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአንዳንድ ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በያበሎ እና ኦቦመርጋ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገርቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡
Yesterday, most places of the South and Southeast, which are experiencing their second rainy season as well as the West, Central and Northwest regions of the country experienced cloud coverage. In connection with this, some areas received light to moderate (1-29mm) rainfall. In addition, heavy rainfall of more than 30mm was recorded in Yabelo and Obomerga in 24 hours. On the other hand, the North, Northeast and East regions of the country experienced dry, sunny and windy Bega weather conditions.