Daily Weather Report 25 October 15

Weather Summary for previous day

Oct. 14, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጥቂት ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቅዳሜ ገበያ፣ ኮበን፣ መንደር 11፣ ቢላምቢሎ እና ያንፋ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡

Yesterday, the southern and southeastern, western and northwestern regions of our country, which are experiencing their second rainy season of the bega, had cloud cover. In connection with this, light to moderate (1-29mm) rainfall was recorded in a few places. Additionally, heavy rainfall of more than 30mm was recorded in Kidame Gebeya, Koben, Village 11, Bilambilo and Yanfa within 24 hours. On the other hand, the central and eastern parts of the country experienced dry, sunny and windy bega weather.

Weather Forecast for next day

Oct. 16, 2025

በነገው ዕለት ለበጋ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ላይ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩልም በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማኦኮሞ፣ መተከል፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ የማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ የማዕከላዊ፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የሻምቡ፣ ጊዳአያና፣ ሊሙ፣ ሳሲጋ፣ ነቀምቴ፣ ጮራ፣ ቀርሳ እና ኮፈሌ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡

Weather conditions conducive to the onset of bega rains will continue to strengthen in the southern and southeastern regions of the country, which are in the second rainy season of the bega. In this regard, the zones of Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedio of the Southern Ethiopian Region; the zones of Sidama Region; the zones of Fafen, Liben, Dawa, Afder, Shebele, Korahe, Nogob, Jarar, Dolo and Erer zones; West Arsi, Bale and East Bale, Borena and East Borena, Guji and West Guji zones of Oromia region will experience light to moderate rainfall (1-29 mm) at many places. On the other hand, there will be heavy cloud cover over the western, southwestern and eastern parts of the country. Therefore, the zones of Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horogudru, Kelem, West and East Wellega, North, West and South West Shewa, Arsi, West and East Hararge; Addis Ababa; Harar; the zones of Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta; the zones of Gurage, Silte, East Gurage, Kebena Special Zone, Hadiya, Marekko Special Zone, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro; Maokomo, Metekele, Asosa and Kamash zones; Majang, Agnuak and Itang zones; Central, North and South Gondar, Awi zone, North, West and East Gojjam zones will experience light rain at some places. In addition, based on the intensifying weather events, some areas of Shambu, Gidayana, Limu, Sasiga, Nekemte, Chora, Kersa and Kofele will experience heavy rainfall within 24 hours. On the other hand, the central and northeastern parts of the country will experience dry, sunny and windy summer weather.