Daily Weather Report 25 October 14
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ መካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡
Yesterday, the south and southeast, which are in their second rainy season of the Bega, as well as the northwest, west, central, and east areas of our country, had cloud coverage. As a result, some areas received light to moderate (1-29 mm) rainfall. On the other hand, the northeast parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ዶሎ፣ ጃራር፣ ፋፈን እና ኤረር ዞኖች በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተመሳሳይም በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ጠንካራ የደመና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማኦኮሞ፣ መተከል፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ የማጃንግ፣ አኙዋክ እና ኢታንግ ዞኖች፤ የደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጅማ አርጆ፣ ኑኑቁምባ፣ ቦነያ ቦሼ፣ ጎቡሰዮ፣ በባኮቲቤ፣ በደሌ፣ ጮራ፣ ቦረቻ፣ ሲግሞ፣ ጌራ፣ ሸበሶምቦ፣ ሰቃ ጮቆርሳ፣ ማንቾ፣ ቀርሳ፣ ቦቶርጦላይ፣ ሳይለም፣ ገሻ፣ ለሞ፣ ሶሮ፣ ጠምባሮ፣ ካቻብራ፣ ባዳዋቾ፣ ዳሞትፑላሳ፣ ሆኮ፣ አሮሬሳ እና ኮኮሳ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For the coming day, the south and southeast parts of our country, which are in their second rainy season of Bega, will have widespread cloud coverage. Along with this, from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, west Arsi, Bale and east Bale zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedeo zones; Sidama region zones; from Somali region Liben, Dawa, Shebelle, Korahe, Nogob, Dollo, Jarar, Fafen and Erer zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. Similarly, strong cloud accumulation is anticipated over the western, southwestern, and eastern parts of the country. Consequently, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horro Guduru, Kelam, west and east Wellega, north, west and southwest Shewa, Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro and Konta zones; Gurage, Silte, east Gurage, Kebena special zone, Hadiya, Mareko special zone, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; Mao Komo, Metekel, Asossa and Kamashi zones; Majang, Agnuak and Itang zones; south Gondar, Awi zone, north, west and east Gojjam zones will receive light rain at some places. Additionally, based on the intensifying weather events, heavy rainfall is expected in Jimma Arjo, Nunu Kumba, Boneya Boshe, Gobuseyo, Bakotibe, Bedele, Chora, Borecha, Sigimo, Gera, Shebe Sombo, Seka Chokorsa, Mancho, Kersa, Botortolay, Sayilem, Gesha, Lemmo, Soro, Tembaro, Kachabira, Badawacho, Damotpulasa, Hokko, Aroresa, and Kokosa within 24 hours.