Daily Weather Report 25 October 13

Weather Summary for previous day

Oct. 12, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጥቂት ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቡሬ፣ ቅዳሜ ገበያ፣ ዶሎመና እና ነገሌ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡

Yesterday, the second rainy season of the bega had cloud cover over the south and southeast, as well as the west, northwest, and east of our country. In connection with this, light to moderate (1-29mm) rainfall was recorded in a few areas. Additionally, heavy rainfall of more than 30mm was recorded in Bure, Kidame Gebeya, Dolomena and Negele within 24 hours. On the other hand, the central regions of the country experienced dry, sunny and windy summer weather.

Weather Forecast for next day

Oct. 14, 2025

በነገው ዕለት ለበጋ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ተጠናክረዉ ይቀጥላሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ላይ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች የደመና ሽፋን እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በመሆኑም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ የማጃንግ ዞን፤ ሀረር፤ የደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እና ከአፋር ክልል የፋንቲ ዞን ላይ አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በነቀምቴ፣ ሳሲጋ፣ ጨዋቃ፣ መኮ፣ ጮራ፣ ደዴሳ፣ ቀርሳ፣ ሰተማ፣ አጋሮ፣ እነሞር፣ ሚሻ፣ ወልበርግ፣ ብላቴ እና ቦና ዙርያ በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow Weather conditions conducive to the formation of bega rains will continue to strengthen in the southern and southeastern regions of the country, which are in the second rainy season of bega. In this regard, the zones of Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedio of the Southern Ethiopian Region; the zones of Sidama Region; the zones of Fafen, Liben, Dawa, Afder, Shebele, Korahe, Nogob, Jarar, Dolo and Erer zones; West Arsi, Bale and East Bale, Borena and East Borena, Guji and West Guji zones of Oromia region will experience light to moderate rainfall (1-29 mm) at many places. On the other hand, forecast indicates that the western, southwestern and eastern parts of the country will have cloud cover. Thus, the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West and South West Shewa, Horogudru, Kelem, West and East Wellega and West and East Hararge zones; the Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; the Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Marekko Special Zone, Hadiya, Halaba,Yem Special Zone, Kembata and Tembaro; the Metekel, Maokomo, Asosa and Kamash zones; the Majang zone; Harar; South and Central Gondar, North, West and East Gojam, Awi Zone, North and South Wollo Zones and Fanti Zone of Afar Region will experience light rain at a few places due to the occasional strengthening weather events. Additionally, heavy rainfall is expected in the areas of Nekemte, Sasiga, Saltuka, Meko, Chora, Dedesa, Kersa, Setema, Agaro, Enmor, Misha, Wolberg, Blate and Bona within 24 hours.