Daily Weather Report 25 October 12
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በምስራቅ፣ በጥቂት በሰሜን ምዕራብና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሀመሮ፣ ኦበመርጋ እና ጎሬ 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡
Yesterday, there was cloud cover and accumulation across southern and southeastern areas which are their second rainy season of Bega as well as in the western, eastern and a few palces of northwest and northeastern parts of our country. In this regards, light to moderate rainfall (1-29 mm) was recorded in some areas. Additionally, Hamero, Obemerga, and Gore within 24 hours. On the other hand, dry, sunny, and windy weather was observed in the northeast and central parts of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ጥንካሬ የሚኖራቸው ሲሆን በምዕራብ አጋማሽ እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይም የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ አዊ፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች እና በጥቂት የሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ ትግራይ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ ባምቢስ፣ አብራሃሞ፣ ቤጊ፣ ጋወከቤ፣ ጂማሆሮ፣ ዋማ ሃጋሎ፣ ቦነያቦሼ፣ መቱ፣ ያዩ፣ ሁሩሙ፣ ዲዱ፣ ሲግሞ፣ ሰተማ፣ ሜና፣ ሳይለማ፣ ማሻ፣ ጌና እና ካቻብራ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡
For tomorrow, The weather systems that favorable conditions for rain formation will be stronger over in the south and southeast which are in their second rainy season of the Bega, and also there will be cloud cover and accumulation across the western and eastern parts of our country. In this regard, from south Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji, and Gedeo zones; Sidama region; from Somali region Fafen, Liben, Dawa, Afder, Shebelle, Kora, Nogob, Jarrar, Doolo, and Erer zones; from Oromia region; in West Arsi, Bale East, Guji and West Guji, Borena and East Borena, as well as in Jimma, Ilubabor, Buno Dele, Horogudru, Kelem, West and East Wolga, West and Southwest Shewa, West and East Hararge zones; Harar; Dire Dawa; from Benishangul Gumuz region Metekel, Maokomo, Asosa and Kamash zones; from Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang and Majang; from Southwestern Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dauro and Konta; from Central Ethiopia East Gurage, Silte, and Kebena Special Zone; Gurage, Mareko Special Zone, Hadia, Halaba, Yum Special Zone, Kembata, and Tembaro zones; from Amhara region, Western, Northern, Southern, and Central Gondar, Awi, Northern, West and East Gojjam zones, and in some parts of Northwest and Central Tigray will receive light to moderate (1-29 mm) amount rainfall . In addition, Assosa, Bambis, Abrahamo, Begi, Gawokebe, Jimahoro, Wama Hagalo, Bonyaboshe, Metu, Yayu, Hurumu, Didu, Sigmo, Setema, Mena, Saylema, Masha, Gena and Kachabira will receive more than 30 mm of heavy rainfall within 24 hours. Meanwhile, in the northeast and central regions of the country, dry, sunny, and windy weather will observed.