Daily Weather Report 25 October 11

Weather Summary for previous day

Oct. 10, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ አጋማሽ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛውና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቻግኒ፣ ጉበቲ፣ ቅዳሜ ገበያ እና ትንሹ ሜጢ 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover and accumulation across southern and southeastern areas which are their second rainy season of Bega as well as in the western half, central, northeastern, and eastern parts of our country. In this regards, light to moderate rainfall (1-29 mm) was recorded in many areas. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded in Chagni, Gubeti, Kidame Gebeya, and Tinshu Metti within 24 hours.

Weather Forecast for next day

Oct. 12, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ከዚህም ባሸገር በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኝው፣ በምስራቅ እና በጥቂት የሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች ላይም የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ የኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ የማዕከላዊ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች፤ የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜን ወሎ እና ዋግኸምራ ዞኖች እና ከአፋር ክልል የቅልበቲ ዞን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በባምቢስ፣ አብራሃሞ፣ በማኦኮሞ ልዩ ዞን፣ አይራ፣ ሊሙ፣ ጎቶጊዳ፣ ባኮቲቤ፣ ዋማ ሃጋሎ፣ ጅማ አርጆ፣ ሰዲጨነቃ፣ መቱ፣ ያዩ፣ ሳይለማ፣ ጌሻ፣ ቢጢ እና ቦሎሶ ሶሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመለክታሉ፡፡

Tomorrow, there will be widespread clouds cover and accumulation over the southern and southeastern areas which are their second rainy season of Bega. Accordingly, the zones of Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji, and Gedeo in the Southern region of Ethiopia, as well as Fafen, Liben, Dawa, Afder, Shebelle, Korahe, Nogob, Jarrar, Doolo, and Erer zones in the Somali region, will receive 1-29 mm of rain. Additionally, there will be cloud cover in the western half, central, eastern, and some northeastern parts. In line with this, the zones of Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West and Southwest Shewa, Horogudru, Kelem, West and East Wollega, and West and East Hararge; Harar; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro, and Konta zones; Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Mareko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro; Metekel, Mao-Komo, Asosa, and Kamashi zones; Itang, Anuak, and Majang zones; central, eastern, southeastern, and southern Tigray zones; western, northern, southern, and central Gondar, northern, western, and eastern Gojjam, Awi, North Wollo, and Waghemra zones, as well as the Kilbeti zone of Afar region, will receive light to moderate rainfall. In addition, our numerical forecast data indicate that in Bambasi, Abrahamo, Maokomo Special Zone, Aira, Limmu, Gutogida, Bakotibe, Wama Hagalo, Jimma Arjo, Sedichenka, Metu, Yayu, Saylema, Gecha, Biti, and Boloso Sore will receive more than 30 mm of heavy rainfall in 24 hours.