Daily Weather Report 25 October 10
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ አጋማሽ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተጠናከረ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቡሬ፣ አትናጎ፣ ያዮ፣ ቅዳሜ ገበያ እና በኮበን በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመካከለኛው፤ ሰሜን ምስራቅ፤ ሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡
Yesterday, the southern, southeastern, and western regions of our country, which are experiencing their second rainy season of the bega, experienced strong cloud cover and accumulation. In connection with this, many areas received light to moderate (1-29mm) rainfall. Additionally, heavy rainfall of more than 30mm was recorded in Bure, Atnago, Yayo, Satu Market and Koben within 24 hours. On the other hand, the central, northeastern, northwestern and eastern regions of the country experienced dry, sunny and windy summer weather.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት ለበጋ ዝናብ መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ አፍደር፣ ሸበሌ፣ ቆራሔ፣ ኖጎብ፣ ጃራር፣ ዶሎ እና ኤረር ዞኖች ፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ላይ በብዙ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ ላይም የደመና ሽፋን እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በመሆኑም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ፤ የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ የኢታንግ፣ አኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ሀረር፤ የምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞኖች፤ የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች እና ከአፋር ክልል የጋቢ እና ሀሪ ዞኖች ላይ አልፎ አልፎ ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ገጽታዎች ላይ በመነሳት ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጥቂት የአሶሳ፣ ሳሲጋ፣ ነቀምቴ፣ ኖኖ ኩምባ፣ መቱ፣ ቡሬ፣ ጮራ፣ ሊሙ ሰቃ እና ወንዶገነት በ24 ሰዓት ውስጥ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow Weather conditions that are conducive to the formation of bega rains will be strongest over the southern and southeastern regions of the country, which are experiencing their second rainy season of the bega. In this regard, the following zones are included in the Southern Ethiopian Region: Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedio; the Sidama Region Zones; the Somali Region: Fafen, Liben, Dawa, Afder, Shebele, Korahe, Nogob, Jarar, Dolo and Erer; the Oromia Region: West Arsi, Bale and East Bale, Borena and East Borena; Guji and West Guji zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall at many places. On the other hand, the forecast indicates that there will be cloud cover over the northwest, west and southwest. Thus, the zones of Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, West, South and West Shewa, Horogudru, Kelem, West and East Wellega and West and East Hararge; the zones of Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta; Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Marekko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro; Metekele, Maokomo, Asosa and Kamash Zones; Itang, Agnewak and Majang Zones; Harar; West and North-West Tigray Zones; West, North, South and Central Gondar, North, West and East Gojam, Awi Zone, North and South Wollo and North Shewa Zones And the Gabi and Hari zones of the Afar region will experience rains based on the weather features that are occasionally strengthening. In addition, a few areas of Asosa, Sasiga, Nekemte, Nono Kumba, Methu, Bure, Chora, Limu Seka and Wondogenet will experience heavy rainfall within 24 hours.