Daily Weather Report 25 October 09
Weather Summary for previous day
በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ ገፅታ ይኖራቸዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ዶሎና ኤረር ዞኖች፣ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሀረር፤ ከትግራይ ክልል የምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ፣ ሀሪ እና አውሲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ ባምቢስ፣ በማኦኮሞ ልዩ ዞን፣ ኩርሙክ፣ አቤ ደንጎሮ፣ ሻምቡ፣ ሳስጋ፣ ለቃ ዱለቻ፣ ጮራ፣ ጅማ አርጆ፣ በደሌ፣ በረቻ፣ ጌራ፣ ሰቃ ጨቆርሳ፣ ቦንጋ፣ ማሻ፣ ሻሸመኔ እና ሐዋሳ ዙርያ 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ አንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመለክታሉ፡፡
For tomorrow, Weather conditions favorable for rains will be more favorable in the south and southeast which are in their second rainy season of the Bega as well as in the western half, central, north-eastern, and eastern parts of our country. In this regard, the zones of Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji, and Gedio in the Southern Ethiopian Region; the zones of Sidama Region; the zones of Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro, and Konta in the Southwestern Ethiopian Region; the zones of Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Mareko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata, and Tembaro in the Central Ethiopian Region; city, Fafen, Jarar, Dolo and Erer zones; from Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horogudru, Kelem, West and East Wellega, West, Southwest and East Shewa, Arsi and West Arsi, Guji and West Guji, West and East Hararge, Bale and East Bale, Borena and East Borena zones; Addis Ababa; Dire Dawa; Harar; from Tigray region, West and North West zones; from Amhara region, North, West South and Central Gondar, North, West and East Gojam, Awi zone, North and South Wallo and North Shewa zones; from Afar region, Gabi, Hari and Awsi zones; from Benishangul Gumuz region, Metekel, Maokomo, Asossa and Kemash zones; From Gambella region, Agnuak, Itang and Majang zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. In addition, according to our numerical forecast data, Asossa, Bambasi, Maokomo Special Zone, Kurmuk, Abe Dengoro, Shambu, Sasiga, Leka Dulecha, Chora, Jimma Arjo, Bedele, Barecha, Gera, Seka Chekorsa, Bonga, Masha, Shashemene and Hawassa areas will receive heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours.
Weather Forecast for next day
በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ አጋማሽ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተጠናከረ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸዉ ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጎበይሬ፣ በያንፎ፣ በሽረ እንደስላሴ፣ በቦሬ፣ በአሶሳ፣ በጉበቲ፣ በነጆ፣ በባህር ዳር፣ በቢላምቢሎ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡
Yesterday, the southern and southeastern which are in their second rainy season and western half of our country experienced heavy cloud coverage and accumulation. In connection with this, light to moderate (1-29mm) rainfall was recorded in many places. In addition, heavy rainfall of more than 30mm was recorded in Gobeyere, Yanfo, Shire Endesilasse, Bore, Asossa, Gubeti, Nedjo, Bahir Dar, and Bilambilo within 24 hours. On the other hand, dry, sunny and windy Bega weather was observed in the north eastern and central parts of the country.