Daily Weather Report 25 October 07

Weather Summary for previous day

Oct. 6, 2025

በትናንትናው ዕለት በምስራቅ እና ደቡብ ትግራይ፣ ምዕራብ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ደቡብ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ ኢትዮጵያ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኙ ሲሆን በላሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the eastern and southern Tigray, western Amhara, Benishangul-Gumuz, Gambella, western, eastern, and southern Oromia, Sidama, and southwestern and southern Ethiopia. In these regrades, light to moderate (1-29 mm) amount rainfall received in some places, while heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded in Lare within a 24-hour period.

Weather Forecast for next day

Oct. 8, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች እንዲሁም በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የጋቢ፣ ፋንቲ፣ ቅልበቲ፣ ሀሪ እና አውሲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ቦረና እና ምስራቅ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ድሬዳዋ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጅ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ሊበን፣ ዳዋ፣ አፍዴር፣ ሸበሌ፣ ቆራሄ እና ዶሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በጭልጋ፣ አበራሀሞ፣ ባምባሲ፣ ኡራ፣ ቤጊ፣ ማናሲቡ፣ አይራ፣ ሳዮኖሌ፣ ሀሩ፣ ጊምቢ፣ ዲጋ፣ አርጆ፣ ዋማሀጋሎ፣ ጨዋቃ፣ በደሌ፣ ደዴሳ፣ ያዩ፣ አልጌ፣ ሁሩሙ፣ ዲዱ፣ ሰተማ፣ ሊሙሰቃ፣ ኖኖቤንጅ እና ማሻ 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, there will be widespread cloudy cover across the southern and southeastern areas which are their second rainy season of Bega as well as in the western half, central, northeastern, and eastern parts of our country. Therefore, from Tigray region western, central, northwestern, eastern, and southeastern zones; from Amhara region western, northern, southern, and central Gondar; north, west, and east Gojjam; Awi zone; North and South Wollo; North Shewa; and Waghemra zones; from Afar region Gabi, Fanti, Kilbeti, Hari, and Awsie zones; from Benshangul-Gumuz region Metekel, Maokomo, Asosa, and Kamash zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Dele, Horogudru, Kelem, West and East Wolga, West, Southwest and East Shewa, Arsi and West Arsi, Gujina and West Guji, West and East Hararge, Bale and East Bale, Borena and Eastern Zones; Addis Ababa, Dire Dawa, and Harar; from Gambella region Agnuwak, Nuwer, Itang, and Majang zones; from Southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Keffa, West Omo, Dauro, and Konta zones; from Central Ethiopia region Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Marrakech Special Zone, Hadia, Halaba, Yum Special Zone, Kembata, and Tembaro zones; from Southern Ethiopia region Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burge, and Gedeo zones; Sidama region zones and from Somali region zones of Citi, Fafen, Jarrar, Erer, Liben, Dawa, Afder, Shebelle, Korahe, and Doolo are expected to receive light to moderate (1 to 29 mm) amount rainfall. Additionally, In Chilga, Abrahamo, Bambasi, Ura, Begi, Aira, Saonole, Haru, Gimbi, Diga, Arjo, Wamahagalo, Chawka, Dedesa, Yayu, Alge, Hurumu, Didu, Setema, Limuska, Nonobenji, and Masha are expected to receive heavy rainfall exceeding 30 mm within 24 hours.