Daily Weather Report 25 October 06

Weather Summary for previous day

Oct. 5, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብና ምስራቅ አማራ፤ በቤንሻንጉል ጉምዝ፤ በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ፤ በጋምቤላ፤ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጥቂት ቦታዎቻቸው ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቡለን እና ቅዳሜ ገበያ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover in West and East Amhara; Benishangul Gumuz; West and South Oromia; Gambella; South Ethiopia and Southwestern Ethiopia. In connection with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in some areas. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Bulen and Kidame Gebeya in 24 hours.

Weather Forecast for next day

Oct. 7, 2025

በነገዉ ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛዉ፣ ምስራቅ እንዲሁም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽና ማኦኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ቄለም፣ ምዕራብ፣ ምስራቅና ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ሀረር፤ ድሬዳዋ፤ ከጋምቤላ ክልል የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስከቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ሁሉም ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የፋፈን፣ ጃራር፣ ኤረር፣ ዳዋ፣ ሊበን፣ ኖጎብ፣ አፍዴር እና ዶሎ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ(1-29 ሚ.ሚ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በመንዲ፣ ነጆ፣ ጉሊሶ፣ አይራ፣ ጊምቢ፣ ሃሩ፣ ላሎቂሌ፣ ጊዳሜ፣ መቱ፣ በደሌ፣ መኮ፣ ጨዋቃ፣ ቦረቻ እና ነቀምቴ በ24 ሰዓት ዉስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover and accumulation in the northwest, west, southwest, central, east, as well as the south and southeast areas of our country, which are experiencing their second rainy season of the bega. In this regard, the West, North West and Central Zones of Tigray Region; North, West, South and Central Gondar, North, West and East Gojam, Awi Zone, North and South Wollo Zones of Amhara Region; Assosa, Metekel, Kamash and Maokomo Zones of Benishangul Gumuz Region; Kelem, West, East and Horogudru Wollega, Ilubabor, Buno, Bedele, Jimma, West and Southwest Shewa, West and East Hararge, Arsi and West Arsi, Bale and East Bale; Guji and West Guji, Borena and East Borena zones; Harar; Dire Dawa; Anwak, Nuer, Itang and Majang zones from Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones from Southwestern Ethiopia region; Gurage, East Gurage, Silte, Kebena Special Zone, Marekko Special Zone, Hadiya, Halaba, M' Special Zone, Kembata and Tembaro Zones; Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedio Zones of the Southern Ethiopian Region; All Zones of Sidama Region; Fafen, Jarar, Erer, Dawa, Liben, Nogob, Afder and Dolo Zones of the Somali Region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, our forecast indicates that Mendi, Nejo, Guliso, Aira, Gimbi, Haru, Laloqile, Gidame, Metu, Bedele, Meko, Chewaka, Borecha and Nekemte will experience heavy rainfall of more than 30 mm within 24 hours.