Daily Weather Report 25 October 01

Weather Summary for previous day

Sept. 30, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ ትግራይ፤ በምዕራብ፣ መካከለኛውና ምስራቅ አማራ፤ በቤንሻንጉል ጉምዝ፤ በምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ እና ምስራቅ ኦሮሚያ፤ በጋምቤላ፤ በደቡብ ኢትዮጵያ፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በብዙ ቦታዎቻቸው ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቡለን፣ ምዕራብ አባያ፣ አርባምንጭ እና ጅንካ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there were cloud cover and accumulations in southern Tigray; western, central and eastern Amhara; Benishangul Gumuz; western, central, southern and eastern Oromia; Gambella; southern Ethiopia; southwestern Ethiopia and Sidama. In connection with this, many of their places received light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Bulen, West Abaya, Arbaminch, and Jinka within 24 hours.

Weather Forecast for next day

Oct. 2, 2025

በነገው ዕለት ለዝናብ መፈጠር ምቹ የሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ እንዲሁም በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ቀጣይነት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ሰሜን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ እና ዋግኸምራ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ ማኦኮሞ፣ አሶሳ እና ካማሽ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን እና ጃራር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በአሶሳ፣ ጃርሶ፣ ጉሊሶ፣ አይራ፣ ያዩ፣ መቱ፣ ቡሬ፣ ሰተማ፣ አጋሮ፣ ሊሙ ሰቃ፣ ኦሞናዳ፣ ሶዶ ዙርያ፣ ቦዲቲ፣ ብላቴ እና አለታወንዶ 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow Weather conditions favorable for rain will continue in the western, central, eastern, and southern and southeastern regions of our country, which are experiencing their second rainy season of the bega. In this regard, the western, central, and northwestern zones of the Tigray region; From the Amhara region, the western, northern, southern and central Gondar, northern, western and eastern Gojam, Awi zone, northern and southern Wollo and Waghemra zones; from the Benishangul Gumuz region, the Metekel, Maokomo, Asosa and Kamash zones; from the Oromia region, the Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Horogudru, Kelem, western and eastern Wollega, northern, western, southwestern and eastern Shewa, Arsi and western Arsi, , Guji and West Guji, West and East Hararge, Bale, Borena and East Borena zones; Addis Ababa; Harar; Anuak, Nuer, Itang and Majang zones from Gambella region; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones from Southwestern Ethiopia region; ; Gurage, Silte, Kebena Special Zone, East Gurage, Marekko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro Zones of Central Ethiopia Region; Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, South Omo and Gedio Zones of Southern Ethiopia Region; Sidama Region Zones and Fafen and Jarar Zones of Somali Region will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Additionally, our forecast data indicates that Assosa, Jarso, Guliso, Aira, Yau, Metu, Bure, Setema, Agaro, Limu Seka, Omonada, Sodo Zuria, Boditi, Bilate and Aletwendo will experience heavy rainfall of over 30 mm within 24 hours.