Daily Weather Report 25 November 30
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ እና በጋምቤላ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያዞ በሲቦ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገርቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በወገልጤና፣ ባቲ፣ በመሀልሜዳ፣ በአለምከተማ፣ በእንዋሪ እና በአርሲ ሮቤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday in southern and southwestern Ethiopia in western Oromia and Gambela the sky was cloudy. Light rain was recorded in and around Sibo. Meanwhile, in the northeastern, central and eastern parts of the country, the weather was hot, sunny and windy. In Wegeltena, Bati, Mehal Meda, Alemketema, Enwari and Arsi Robe, daytime low temperatures were reported below 5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እንዲሁም የጅማና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት በምስራቅ ጎጃም ዞን በጥቂት ስፍራ ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow during the day, cloudy conditions with a chance of light rain are expected in the southern and south-eastern, as well as the western and south-western parts of the country. In addition, light rain showers will occur in a few places of the following zones: from Oromia region Guji and West Arsi zones; from Southern Nations, Nationalities, and Peoples' Region Gamo, Gofa, Basketo and Gedeo zones; zones of Sidama and also the Jimma and Ilubabor zones; from South West Ethiopia Peoples' Region Sheka, Bench Sheko, Keffa, Konta and Dawuro zones; and from Gambela region Agnwuak and Majang zones. Furthermore, assisted by the cloud cover, unseasonal light rain is expected in a few places of the East Gojjam zone. On the other hand, the northern-eastern, eastern and central parts of the country will experience a dry, sunny and windy daytime weather; forecast information indicates the daytime minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius.