Daily Weather Report 25 November 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በምዕራብ ኦሮሚያ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያዞ በቴፒ፣ ጪራ፣ አማን፣ ወላይታ ሶዶ፣ ምዕራብ አባያ እና ሳውላ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገርቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በደብረብርሀን፣ በጨለንቆ፣ በቁልቢ እና በአለም ከተማ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy patches over southern and southwestern Ethiopia and western Oromia. In line with this, light to moderate rain (1–29 mm) was recorded in Tepi, Chira, Aman, Wolayta Sodo, West Abaya and Sawula. Elsewhere in the northeastern, central and eastern parts of the country, the weather was dry, sunny and windy. Daytime minimum temperatures as low as 5°C were recorded in Debre Berhan, Chelenko, Kulubi and Alem Ketema.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂ፣ ባሌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እንዲሁም የጅማና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ከፋ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት ደቡብ ጎንደር፣ደቡብ ወሎ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow during the day there will be cloudy patches in the south and southeast, and likewise in the west and southwest of the country. In connection with this, light rain is expected in some places of the Guji, Bale and West Arsi zones of Oromia; zones of Sidama; the Jimma and Iluababora zones; the Sheka, Bench Sheko and Kaffa zones of Southwest Ethiopia; and the Agnwuak and Majang zones of Gambela. In addition, due to moving cloud cover, light, un seasonal scattered showers are expected in parts of South Gondar, South Wollo and East Gojjam. On the other hand, the northern, eastern and central parts of the country will experience a Bega-like dry, sunny and windy weather pattern, with daytime minimum temperatures forecast to be below 5 degrees Celsius.