Daily Weather Report 25 November 28
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቡለሆራ፣ ቦሬ፣ ዲላ፣ አርባ ምንጭ፣ ሳዉላ፣ ወላይታ፣ ማጂ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ አጋሮ፣ ይርጋለም፣ ጉበቲ እና ትንሹ ሜጢ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በአምባማሪያም፣ አለምከተማ፣ ቡኢ፣ ሐሮማያ፣ ጨለንቆ እና ቁሉቢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the southern, southwestern and western parts of the country had cloud coverage. In this regard, Bulehora, Bore, Dilla, Arba Minch, Sawula, Walaita, Maji, Chira, Jimma, Agaro, Yirgalem, Gubeti, and Tinishu Meti received light to moderate rainfall. Conversely, dry, sunny, and windy Bega weather was observed in the northeastern, central, and eastern parts of the country; the daily minimum temperature was recorded below 5°C in Ambamariam, Alemketema, Bui, Haromaya, Chelenko, and Kulubi.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በደቡብ፣ በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል የጉጂ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ጅማ እና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የባስኬቶ፣ ወላይታ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ እና ዳዉሮ ዞኖች እና ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት በጥቂት የአዊ ዞን፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፤ በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage over the southern, western, and south-western parts of the country. In this respect, from Oromia region Guji, Bale, Arsi, Jimma, and Ilubabor zones; from the south Ethiopia region Basketo, Walaita, and Gedeo zones; Sidama region zones; from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, and Dawuro zones, and from Gambella region Agnuak and Majang zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at a few places. Additionally, due to the cloud coverage, a few areas of the Awi zone, east Gojjam, south Gondar, and south Wollo zones will experience light, unseasonal rainfall. On the other hand, the Bega dry, sunny, and windy weather conditions will be observed in the northeastern, central, and eastern parts of our country; accordingly, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature will drop by 5 degrees Celsius in some areas.