Daily Weather Report 25 November 27

Weather Summary for previous day

Nov. 26, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በሲዳማ፣ በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ እና በጋምቤላ አነስተኛ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያዞ በጎሬ፣ ሊሙገነት፣ አጋሮ፣ ቢላምቢሎ፣ ቦሬ፣ ፉኝዶ፣ መንደር-7፣ ጉበቲ፣ ይርጋለም እና ሳውላ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በጥቂት ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, light clouds were observed in southern and southwestern Ethiopia, Sidama, western and southern Oromia, and Gambella. In this regard, light to moderate rainfall (1–29 mm) was recorded in Gore, Limuganet, Agaro, Bilambilo, Bore, Fundo, Village-7, Gubeti, Yirgalem, and Sawla. In contrast, dry, sunny, and windy Bega weather prevailed in the northeastern, central, and eastern parts of the country, while a few highland areas experienced daily minimum temperatures below 5 °C.

Weather Forecast for next day

Nov. 28, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ እና አፍዴር ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት የባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ፣ ጅማ፣ ኢሉባቦር እና ቡኖበደሌ ዞኖች፤ የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እንዲሁም የምስረቅ ጎጃም ዞን በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For the next day, there will be cloud cover in the south and southeast, which are the second rainy season of Bega. In this context, from South Ethiopia region Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, and Gedeo zones; the zones of the Sidama region; from Somali region Liben, Dawa, and Afder zones; and from Oromia region zones Borena, east Borena, Guji, and west Guji zones will receive light rainfall in a few places. Additionally, due to occasional cloud cover, in a few places of Bale and east Bale, Arsi and west Arsi, west and east Hararge, Jimma, Ilubabor, and Buno Bedele zones; Sheka, Bench Sheko, Kefa, west Omo, Dawa, Agnuak, Majang, and east Gojjam zones will have light to moderate (1-29 mm) unseasonal rainfall. On the other hand, in the northeastern, eastern, and central parts of the country will be dry, sunny, and windy weather condition, and the daily minimum temperatures dropping below 5 degrees Celsius.