Daily Weather Report 25 November 26
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ ምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ምዕራብ አማራ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሙጊ፣ መንደር-13 እና ሐዋሳ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለባቸው ሲሆን፤ በጥቂት የምስራቅ አማራ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over Gambella, Sidama, west and south Oromia, southwest Ethiopia, and the west Amhara region. Consequently, Mugi, Mender-13, and Hawassa received light to moderate rainfall. Conversely, dry, sunny, and windy of Bega weather condition were observed over the north-east, central, and east parts of the country; as a result, the daily minimum temperature was recorded below 5°C in some areas of east Amhara and the highlands of the eastern areas of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር እና ቡኖ በደሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል በጥቂት የሊበን ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት በጥቂት የአዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፣ ደቡብ ወሎ፣ አርሲ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage over the south and southeast, which are the second rainy season of the Bega, as well as the west and southwest parts of the country. In this regard, from Oromia region Guji and west Guji, east Borena, west Arsi, Bale and east Bale zones, as well as Jimma, Ilubabor and Buno Bedele zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Burji, Konso, Kore, Gardula, south Omo and Gedeo zones; Sidama region zones; from Somali region in few areas of Liben zone; from Gambella region Agnuak and Majang zones; from south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from the central Ethiopian region Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at a few places. Moreover, due to occasional cloud coverage, a few areas of Awi zone, west and east Gojjam, south Gondar, south Wollo, Arsi, and west Hararge zones will experience light unseasonal rainfall. On the other hand, dry, sunny, and windy Bega weather will prevail in the northeast, central, and eastern portions of our country; accordingly, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature will drop 5 degrees Celsius.