Daily Weather Report 25 November 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጥቂት የሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጎንደር፣ ሽንዲ፣ ቡሬ እና ነጆ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በወገልጤና፣ አለምከተማ፣ ደብረብርሀን፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ ጨለንቆ፣ ጋሸና እና በቁሉቢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over few parts of the northwest, west and southwest of the country. In this regard, Gondar, Shendi, Bure and Nedjo received light rain. On the other hand, the northeast, central and eastern parts of the country experienced dry, sunny and windy Bega weather; in association with this the daily minimum temperature recorded below 5°C in Wegeltena, Alemketema, Debrebrehan, Bishoftu, Bui, Chelenko, Gashena and Kulubi.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች እና በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ በጥቂት የኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ እና ቀለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂ፣ ኮሬ፣ ጋርዱላ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን እና አፍደር ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የአዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፣ አርሲ፣ ኤረር፣ ሐረር፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
For the next day, the south and south eastern parts of our country, which are in their second rainy season of the Bega, and the western, southwestern, and eastern parts of the country will have cloud coverage. In this respect, from Oromia region Guji and west Guji, east Borena, west Arsi, Bale and east Bale zones, as well as Jimma, few areas of Ilubabor, Buno Bedele and Kelam Wellega zones; from south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, Burji, Kore, Gardula, south Omo and Gedeo zones; Sidama region zones Dawa, Liben and Afder zones of Somali region; from Gambella region Agnuak and Majang zones; from south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from central Ethiopian region Hadiya, Gurage, Silte, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall at some places. Besides, due to the strengthening weather events, a few areas of the Awi zone, west Gojjam, south Gondar, Arsi, Erer, Harar, west and east Hararge zones will experience light unseasonal rainfall. On the other hand, the northeast and central portions of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather; accordingly, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature cloud drop 5 degrees Celsius.