Daily Weather Report 25 November 24

Weather Summary for previous day

Nov. 23, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በምዕራብ አማራ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በምስራቅ የሀገርቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በወገልጤና፣ በባቲ፣ በመሀልሜዳ፣ በወረኢሉ፣ በመንዲዳ፣ በየትኖራ፣ በእንዋሪ፣ በደብረብርሀን፣ በጨለንቆ፣ በቁልቢ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በእምድብር፣ በጂማ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover over the southern and southwestern Ethiopia, western Oromia, Gambella, and western Amhara. In contrast, dry, sunny, and windy Bega weather was observed in the northeast, central, southern highlands, and eastern parts of the country. In line with this, the daily minimum temperature dropped below 5 degrees Celsius in Wegeltena, Bati, Mehalmeda, Wereilu, Mendida, Yetnora, Enwari, Debrebrihan, Chelenko, Kulubi, Bishoftu, Bui, Emdibir, Jimma, Arsi Robe, Haromaya, and Jigjiga.

Weather Forecast for next day

Nov. 25, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የሊበን ፣ ሸበሌ እና አፍዴር ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ኮሬ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን እና ከምባታ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት ደቡብ ወሎ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover in the south and southeast, which are the second rainy season of Bega, as well as in the western and southwestern parts of the country. In this regard, from Oromia region Guji and West Guji, Bale and East Bale, West Arsi, Borena and East Borena zones; from Somali region Liben, Shebelle, and Afder zones; from southern Ethiopia region Gamo, Gofa, Basketo, Kore, Burji, and Gedeo zones; the Sidama zone, and the Jimma, Ilubabor, Kelem Wellega, Sheka, and Bench Sheko zones of the southwest region of Ethiopia region; from Gambella region Agnuak and Majang zones and from central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, and Kembata zones, will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in some areas. Additionally, due to occasional cloud cover, light unseasonal rain may occur in a few places in the South Wollo and East Gojjam zones. On the other hand, the northeast, east, and central parts of the country will be dry, sunny and windy weather condition and the daily minimum temperatures expected to drop below 5 degrees Celsius.