Daily Weather Report 25 November 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፥በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በምስራቅ የሀገርቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተውሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም መሀልሜዳ፣ ቡኢ፣ ዋጋልቴና፣ ኤኑዋሪ፣ ቢሾፍቱ፣ ባሌ ሮቤ፣ አርሲ ሮቤ እና ቁሉቢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ የተመዘገቤ ስሆን ጨለንቆ እና ደብረ ብርሃን ከ 0 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡በሌላ በኩል በምዕራብ አማራ በጥቂት ቦታዎቻቸው የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ በመሆኑም መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡
Yesterday, the northeast, central, and southern highlands and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy summer weather. In this regard, Mehalmeda, Bui, Wagaltena, Enuari, Bishoftu, Bale Robe, Arsi Robe, and Qulubi recorded daily minimum temperatures below 5 degrees Celsius, while Chelenko and Debre Berhan recorded minimum temperatures below 0 degrees Celsius. On the other hand, there was cloud cover in a few places in western Amhara. As a result, Dangila received moderate (1-29 mm) rainfall.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በወገልጤና፣ አምባማርያም፣ ባቲ፣ መሀልሜዳ፣ ጋሸና፣ ደብረብርሀን፣ እንዋሪ፣ አለምከተማ፣ ሾላገበያ፣ ደባርቅ፣ ቢሾፍቱ፣ ቡኢ፣ አርሲ ሮቤ፣ ባሌሮቤ፣ ሐሮማያ፣ ጨለንቆ እና ጂጂጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ የሚመዘገብ ሲሆንና፤ የሌሊትና የማለዳው ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሸካ እና ከፋ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For the next day, the northeast, east, southern highlands, and central parts of the country will be dominated by dry, sunny, and windy weather. In line with this, Wogeltena, Ambamariam, Bati, Mehalmeda, Gashena, Debre Birhan, Enuwari, Alem Ketema, Shola Gebaya, Debarq, Bishoftu, Bui, Arsi Robe, Bale Robe, Haromaya, Chelenko, and Jijiga will record a minimum temperature of below 5 degrees Celsius, and the night and morning cold will continue. On the other hand, there will be cloud cover over the western and southwestern parts of the country. In this regard, light rain will be expected in the Ilubabor, Kelem, and West Wellega zones of the Oromia region; the Sheka and Kefa zones of the Southwestern Ethiopia region; and the Agnuwak zone of the Gambella region.