Daily Weather Report 25 November 19

Weather Summary for previous day

Nov. 18, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በምዕራብ አማራ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በ ቻግኒ፣ ኦንጋ፣ መንደር 13፣ አይሺ፣ ኪዳሜ ገበያ፣ ኦቦ መርጋ፣ ቡልኪ፣ ላይበር፣ ጎሬ፣ አርባ ምንጭ እና ቢላቴ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቡሬ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገርቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ ደባርቅ፣ አለም ከተማ፣ ደብረ ብርሀን፣ ሾላ ገበያ፣ ሐሮማያ፣ ጅግጅጋ፣ ጉንዶ ቤሬት ፣ቡኢ እና ጨለንቆ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡

Yesterday, there was cloud coverage in southern and southwestern Ethiopia, western Oromia, Gambella and western Amhara. In this regard, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Chagni, Onga, Village 13, Aishi, Kidame Gebeya, Obo Merga, Bulki, Laiber, Gore, Arbaminch and Bilate. In addition, heavy rainfall of more than 30 mm was recorded in Bure in 24 hours. On the other hand, dry, sunny and windy bega weather was observed in the north eastern, central and eastern parts of the country. In line with this Debark, Alem Ketema, Debre Birhan, Shola Gebeya, Haromaya, Jigjiga, Gundo Beret, Bui and Chelenko the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

Nov. 20, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ቦረና እና ምስራቅ ቦረና ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን እና አፍዴር ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮሬ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳውሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ማኦኮሞ ዞን በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት በሰሜን፣ ደቡብና ማዕከላዊ ጎንደር እና ምስራቅና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For tomorrow, there will be cloud coverage over the southern and southeastern, which are experiencing their second rainy season of the bega as well as western and southwestern parts of the country,. In connection with this, the Guji and West Guji, Bale, West Arsi, Borena and East Borena zones of the Oromia region; the Dawa, Liben and Afder zones of the Somali region; the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, South Omo, Kore, Burji and Gedio zones of the Southern Ethiopia region; the Sidama region zones as well as the Jimma, Ilubabor, Kelem and West Wellega zones; the Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo and Dawro zones of the Southwestern Ethiopia region; The Agnuak, Itang and Majang zones of Gambella region and the Maokomo zone of Benishangul Gumuz region will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall at isolated places. In addition, due to the occasional cloud cover, light to unseasonal rainfall will occur at isolated places in North, South and Central Gondar and East and West Gojjam zones. On the other hand, dry, sunny and windy weather will be observed in the North-East, East and Central parts of the country; the forecast data indicates that the minimum temperature of the day will be recorded below 5 degrees Celsius.