Daily Weather Report 25 November 18

Weather Summary for previous day

Nov. 19, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብና ደቡብምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በምዕራብ አማራ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአይከል፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ ቻግኒ፣ አይራ፣ ደምቢዶሎ፣ ቢላምቢሎ፣ ፉጎሎቃ፣ መቱ፣ ባሮቦንጋ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ኦንጋ፣ መንደር 13፣ ወላይታ፣ ሳውላ፣ ብላቴ እና ዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገርቱ አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በወገልጤና፣ አለም ከተማ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላ ገበያ፣ እንዋሪ፣ ቡኢ እና ጨለንቆ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡

Yesterday, there was cloud cover across the southern and southwestern Ethiopia, western Oromia, Gambella, and western Amhara. In this context, light to moderate rainfall (1-29 mm) were received in Aykel, Debark, Gondar, Chagni, Aira, Dembidolo, Bilambilo, Fugoleka, Metu, Barobonga, Gambella, Fugnido, Onga, Village 13, Wolayta, Sawla, Bilatte, and Dilla. On the other hand, dry, sunny, and windy Bega weather condition was observed in the northeast, central, and eastern parts of the country and the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius in Wegeltena, Alemketama, Debre Birhan, Shola Gebeya, Enewari, Bui and Chelenko.

Weather Forecast for next day

Nov. 19, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ አፍዴር፣ ኖጎብ፣ ሸበሌ እና ቆራሄ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ እና ከፋ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ፣ ኢታንግ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የአሶሳ እና ማኦኮሞ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት በአዊ፣ ሰሜንና ምዕራብ ጎጃም እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover in the south and southeast, as well as in the western and southwestern parts of the country, which are the second rainy season of Bega. In this regards, from Somali region in Liben, Afder, Nogob, Shebelle, and Korahe; southern Ethiopian region Gofa, Basketo, South Omo, and Gedo zones; the Sidama region zones; from Oromia region Guji and west Guji zones; as well as Jimma, Ilubabor, Kelem, and West Wellega; from Southwest region Bench Sheko, Sheka, and Kefa zones; and from Gambella region Agnuwak, Itang, and Majang zones; and from Benishangul-Gumuz region Asossa and Maokomo zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) in some areas. Additionally, due to scattered cloud cover, there will be light unseasonal rain in a few places of Awi, northwest Gojjam, and south Gondar zones. On the other hand, the northeast, east, and central parts of the country will experience dry, sunny, and windy summer weather, and the daily minimum temperatures drop below 5 degrees Celsius.