Daily Weather Report 25 November 17
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በጥቂት የሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጎንደር፣ አይከል፣ አዲስ ዘመን፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ አይራ፣ ጎሬ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ኮባን፣ ኩሚ፣ ሙጊ፣ ሲቦ፣ ትንሹ ሜጢ፣ መንደር-11፣ ሳዉላ፣ ይርጋለም እና ዲመካ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በአዴት እና ኦቦመርጋ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over a few areas of the northwest, west, and south of the country. In line with this, Gondar, Ayikel, Addis Zemen, Dangila, Chagni, Aira, Gore, Gambella, Fugnido, Koban, Kumi, Mugi, Sibo, Tinishu Meti, Mender-11, Sawula, Yirgalem, and Dimeka received light to moderate rainfall, while heavy rainfall was recorded in Adet and Obomerga. On the other hand, the northern, central, northeastern, and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ፤ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል በጥቂት የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ በጥቂት የምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን፣ አፍደር እና ዶሎ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ፣ ኮንታ፣ አሶሳ፣ ማኦኮሞ፣ ማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት በጥቂት የአዊ ዞን፣ ምዕራብ ጎጃም እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
For the next day, the south and southeast parts of our country, which are in their second rainy season of the Bega, will have cloud coverage. In this respect, from Oromia region few areas of Guji and west Guji, Borena and east Borena, west Arsi and Bale zones; from south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedeo zones; Sidama region zones and from Somali region Dawa, Liben, Afider and Dollo zones will receive light. As well, Jimma, Ilubabor, Kelam Wellega, Bench, Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro, Konta, Asossa, Mao Komo, Majang and Agnuwak zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall at a few places. Besides, due to the strengthening weather events, a few areas of Awi zone, west Gojjam and central Gondar zones will experience light unseasonal rain. On the other hand, the northeast, central and eastern parts of the country will experience dry, sunny and windy Bega weather condition; forecast information indicates that the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius.