Daily Weather Report 25 November 16

Weather Summary for previous day

Nov. 15, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብና ደቡብምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በምዕራብ አማራ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ምዕራብ ኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በምዕራብ አማራ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአይከል፣ ደባርቅ፣ ደብረታቦር፣ ቻግኒ፣ አይራ፣ ጎሬ፣ ኩሚ፣ ትንሹሚጢ እና ሙጊ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገርቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በአምባ ማርያም፣ አለም ከተማ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላ ገበያ፣ እንዋሪ፣ ቡኢ እና አርሲ ሮቤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡

Yesterday, there was cloud cover in southern and southwestern Ethiopia, western Oromia, Gambella, and western Amhara. In this regard, light rainfall was recorded in Aykel, Debark, Debretabor, Chagni, Aira, Gore, Kumi, Tineshumetti, and Mugi. On the other hand, the weather was dry, sunny, and windy in the northeast, central, and eastern parts of the country, while the daily temperatures were recorded below 5 degrees Celsius in Amba Mariam, Alem City, Debrebrihan, Shola Market, Enwari, Bui, and Arsi Robe.

Weather Forecast for next day

Nov. 17, 2025

በነገዉ ዕለት በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፤ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስከቶ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳም ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም የጅማ፤ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች፤ የአኝዋክ፣ ኢታንግና ማጃንግ ዞኖች፤ የአሶሳና ማኦኮሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች በመነሳት በአዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸዉ ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋልባቸዉ ሲሆን፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the southern and southeastern parts of the country. In this regard, light rainfall is expected from Oromia region, west Arsi, Bale, Borena, Guji, and west Guji zones; from southern Ethiopia region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Gardula, Kore, Alle, South Omo, and Gedeo zones, the zones of the Sidama region, and from Somali region Dawa and Liben zone. In addition, there will be cloud cover in the western and southwestern parts of the country. Thus, in Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelem, and west and east Wellega zones; Sheka, Kefa, West Omo, Dawro, and Konta zones; Agnuak, Itang, and Majang zones, as well as Asossa and Maokomo zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Meanwhile, due to the intensification of weather activity, light unseasonal rainfall will receive in a few places of Awi zone, western, northern, and eastern Gojjam, and northern and southern Gondar zones. On the other hand, the northeast, eastern, and central parts of the country will experience dry, sunny, and windy summer conditions and also the forecasts indicate that temperatures will drop below 5 degrees Celsius.