Daily Weather Report 25 November 15

Weather Summary for previous day

Nov. 14, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በደቡብምዕራብ፣ በምዕራብ እና በሰሜንምዕራብ የሀገርቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጎንደር፣ አይከል፣ ደብረታቦር፣ ላሊበላ፣ ደብረማርቆስ፣ አይራ፣ ነቀምቴ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጋምቤላ፣ ቅዳሜገበያ፣ ኩሚ፣ ኦንጋ፣ ትንሹሚጢ፣ ቡሬ፣ ጭራ እና ዲላ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገርቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሐያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለባቸዉ ሲሆን፤ በወገልጤና፣ አምባ ማርያም፣ አለም ከተማ፣ ደብረብርሀን፣ ሾላ ገበያ፣ ቡኢ፣ ጨለንቆ እና አርሲ ሮቤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡

Yesterday, there was cloud cover across the south and southeast, as well as in the southwest, west, and northwest parts of the country. Accordingly, in Gondar, Aykel, Debre Tabor, Lalibela, Debre Markos, Aira, Nekemte, Bedele, Gore, Gambella, Kidame Gebeya, Kumi, Onga, Tinshu Mitti, Bure, Chira, and Dilla received light to moderate rainfall (1-29 mm). Meanwhile, dry, sunny, and windy summer weather were observed in the northeast, central, and eastern regions of the country; and the daily minimum temperature recorded below 5 degrees Celsius in Wogeltena, Amba, Mariyam, Alem Ketema, Debre Birhan, Shola Gebeya, Bui, Chelenko, and Arsi Robe.

Weather Forecast for next day

Nov. 16, 2025

በነገዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስከቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ ሁሉም የሲዳም ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የአፍደር፣ ሸበሌና ዶሎ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲና አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የጅማ፤ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች፤ የሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ የአኝዋክ፣ ኢታንግና ማጃንግ ዞኖች፤ የአሶሳና ማኦኮሞ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት የአረሲ፣ ምዕራብ ሀረርጌ፣ የአዊ ዞን፣ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸዉ ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋልባቸዉ ሲሆን፤ በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the southern and southeastern parts of the country which are in their second rainy season of the Bega. In association with this, from southern Ethiopian region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, Alle, South Omo, and Gedeo zones; all zones of the Sidama region; from Somali region in Afder, Shebelle, and Doolo zones; from Oromia region western Arsi, Bale and east Bale, Guji and western Guji zones will receive light rain. In addition, in Jimma, Ilubabor, Buno Dele, Kelem, West and East Wolga zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones, Agnuwak, Itang and Majang zones, Asossa and Maokomo zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm). Besides this, due to cloud cover, areas in Arsi, West Hararge, Awi Zone, and the West, North, and East Gojjam as well as the North and South Gondar zones are likely to receive light, unseasonal rainfall in a few places. On the other hand, the eastern, eastern, and central parts of the country will experience dry, sunny, and windy weather, with forecasts indicating that the minimum temperature in some areas will drop below 5 degrees Celsius.