Daily Weather Report 25 November 14
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሞያሌ፣ ዲላ፣ ቢላቴ፣ አማን፣ ዲመካ፣ ፉኝዶ፣ ጭራ፣ ጎሬ፣ መቱ፣ አትናጎ፣ ቢላምቢሎ፣ ፉጎሌቃ፣ ያንፋ፣ ያዮ፣ ቅዳሜገበያ፣ ሲቦ፣ አዲስ ዘመን፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ ላይበር እና ዳባት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በሙጊ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በጥቂት የምስራቅ አማራ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the southern, southwestern, and western parts of the country. In this respect, Moyale, Dilla, Bilate, Aman, Dimeka, Fugnido, Chira, Gore, Mettu, Atinago, Bilambilo, Fugoleka, Yanfa, Yayo, Kidame Gebeya, Sibo, Addis Zemen, Dangila, Chagni, Laiber, and Dabat received light to moderate rainfall, while heavy rainfall was recorded in Mugi. Conversely, the northeastern, central, and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather. Besides, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in a few areas of east Amhara and the highlands of the eastern part of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል በጥቂት የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ እንዲሁም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ በጥቂት የምዕራብ ሸዋ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የአሶሳ፣ መተከል እና ማኦኮሞ ዞኖች፤ የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች፤ የአዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
For the coming day, the south and southeast parts of our country, which are in their second rainy season of the Bega, will have cloud coverage. In this regard, from Oromia region in a few areas of Guji and west Guji, Borena and east Borena, west Arsi, Bale and east Bale zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedeo zones, and Sidama region zones will receive light rain. Likewise, Jimma, Ilubabor, Kelam, west and east Wellega, a few areas of west Shewa and west Hararge zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro, and Konta zones; Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; Asossa, Metekel and Mao Komo zones; Majang and Agnuwak zones; Awi zone and west Gojjam zones will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall at a few places. On the other hand, the northeast, central, and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather conditions; the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius, according to weather forecast information.