Daily Weather Report 25 November 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ፣ በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገርቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዠም በአድግራት፣ ጎንደር፣ ዳንግላ፣ ንፋስ መዉጫ፣ ላይበር፣ አሶሳ፣ ነጆ፣ ደንብ ዶሎ፣ ጎሬ፣ ቡሬ፣ ጭራ፣ ጋቲራ፣ አርጆ፣ አማን፣ እሮሚች፣ አሽ፣ ጎብቲ፣ ሙጊ፣ ሆንጋ፣ ሲቦ፣ ሀገሬ ሰላም፣ ቢላምቢሎ፣ ዎርክአምባ፣ ፉጎሌቃ፣ ያንታ፣ ያዮ፣ ዲመካ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገርቱ አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዋለባቸዉ ሲሆን በአ/ማርያም፣ በጨለንቆ፣ በአለም ከተማ፣ በሾላ ገበያ፣ በቡይ እና በቁልብ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡
Yesterday, there was cloud coverage over the south and southeast, which are in their second rainy season of the Bega, as well as the west, west and northwest regions of the country. In addition, Adigrat, Gondar, Dangila, Nefas Mewucha, Laiber, Asossa, Nedjo, Dembi Dolo, Gore, Bure, Cira, Gatira, Arjo, Aman, Eremich, Ashi, Gubeti, Mugi, Onga, Sibo, Hagere Selam, Bilambilo, Workamba, Fugoleka, Yanfa, Yayo and Dimeka received light to moderate (1-29mm) rainfall. On the other hand, dry, sunny and windy summer weather was observed in the north, northeast and east of the country, with the lowest daily temperature recorded below 5 degrees Celsius in A/Mariam, Chelenko, Alem Ketema, Shola Gebeya, Bui and Qulbi.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና በደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስከቶ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ደቡብ ኦሞና ጌዲኦ ዞኖች፤ ሁሉም የሲዳም ክልል ዞኖች፤ ከሶማሌ ክልል የአፍደር፣ ሸበሌና ዶሎ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲና አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፤ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን በመነሳት በጅማ፤ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ የአኝዋክ፣ ኑዌር፣ ኢታንግና ማጃንግ ዞኖች፤ የአሶሳ፣ መተከል፣ ካማሽና ማኦኮሞ ዞኖች፤ የደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ ምስራቅ እና መካከለኛ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋልባቸዉ ሲሆን፤ በጥቂት ቦታዎቻቸዉ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
For tomorrow, there will be cloud coverage over the southern and southeastern regions of our country, which are in their second rainy season of the Bega. In this regard, the Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Konso, Burji, Gardula, Kore, Ale, South Omo and Gedio zones of the Southern Ethiopian Region; all Sidam Region zones; Afder, Shebele and Dolo zones of the Somali Region; West Arsi and Arsi, Bale and East Bale of the Oromia Region; Guji and West Guji zones will experience light rain. In addition, due to the cloud coverage, Jimma; Ilubabor, Buno Bedele, Horo Guduru, Kelem, West and East Wellega; Bench Sheko, Sheka, Kefa, West Omo, Dawro and Konta zones; Gurage, East Gurage, Silte, Kebena Special Zone, Mareko Special Zone, Hadiya, Halaba, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro Zones; Angewak, Nuer, Itang and Majang Zones; Asossa, Metekel, Kamashi and Maokomo Zones; South Gondar, Awi Zone, West and East Gojam Zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at some places. On the other hand, dry, sunny and windy weather will be observed in the north, east and central parts of the country; numerical forecast data indicates that the minimum temperature of the day will be below 5 degrees Celsius at some places.