Daily Weather Report 25 November 09

Weather Summary for previous day

Nov. 8, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በያቤሎ፣ ቡሌሆራ፣ ቡርጂ፣ ኮንሶ፣ ዲላ፣ አማን፣ ማሻ፣ ጭራ፣ ጎሬ፣ በደሌ፣ አርጆ፣ ነቀምቴ፣ ሻምቡ እና መንደር-11 ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡

Yesterday, cloud coverage was over the southern, southwestern, and western parts of the country. Consequently, Yabelo, Bulehora, Burji, Konso, Dilla, Aman, Masha, Chira, Gore, Bedele, Arjo, Nekemte, Shambu, and Mender-11 received light to moderate rainfall. Conversely, the northern, central, northeast, and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather conditions.

Weather Forecast for next day

Nov. 10, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል በጥቂት የዳዋ ዞን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ፣ ኮንታ፣ ሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ፣ ጠምባሮ፣ ማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል።

For the coming day, the south and southeast parts of our country, which are in their second rainy season of the Bega, will have cloud coverage. In this regard, from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, west Arsi and Bale zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji, and Gedeo zones; Sidama region zones, and a few areas of the Somali region in the Dawa zone will experience light rain. Besides, there will be cloud coverage over the western and southwestern parts of the country, while the zones of Jimma, Ilubabor, Kelam Wellega, Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro, Konta, Hadiya, Yem special zone, Kembata, Tembaro, Majang, and Agnuwak will experience light to moderate (1-29 mm) rainfall. On the other hand, the northeastern, central, and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather conditions.