Daily Weather Report 25 November 08

Weather Summary for previous day

Nov. 7, 2025

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት ደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ቡለሆራ፣ ቦሬ፣ ባሌሮቤ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ፣ ጂንካ፣ ሳዉላ፣ ዲላ፣ ምዕራብ አባያ፣ ቴፒ፣ ተርጫ፣ ጎሬ፣ ጅማ፣ ጋምቤላ፣ ጉበቲ እና ኩሚ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ ያገኙ ሲሆን በማጂ እና በሙጊ ደግሞ ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over the south and southeast, which are in their second rainy season, as well as the southwest parts of the country. In this regard, Moyale, Yabelo, Bulehora, Bore, Balerobe, Konso, Burji, Jinka, Sawula, Dilla, West Abaya, Tepi, Tercha, Gore, Jimma, Gambella, Gubeti, and Kumi received light to moderate (1-29 mm) rain, Heavy rainfall is recorded in Maji and Mugi. In contrast, the northeast, central, and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy Bega weather. Additionally, the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius in a few highlands of the country.

Weather Forecast for next day

Nov. 9, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮሬ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን እና አፍደር ዞኖች በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን ላይ በመነሳት በጥቂት የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳዉሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የሀድያ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የማጃንግ እና አኙዋክ ዞኖች ቀላል መጠን ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፤ በአንዳንድ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, the southern and southeastern parts of the country, which are in their second rainy season of the Bega, will have cloud coverage. In this respect, from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, west Arsi, Bale and east Bale zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Kore and Gedeo zones; Sidama region zones and the Dawa, Liben and Afder zones of the Somali region will experience light rain at some places. Moreover, based on the cloud cover, a few Jimma, Ilubabor, Kelam Wellega, Buno Bedele, Arsi, west and east Hararge zones; Bench Sheko, Sheka, Kefa, west Omo, Dawuro, and Konta zones; Hadiya, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; Majang and Agnuwak zones will experience light rainfall. On the other hand, dry, sunny, and windy weather will prevail in the north, northeast, central, and eastern parts of the country; the numerical weather forecast indicates that the daily minimum temperature will be recorded below 5 degrees Celsius in some highlands.